1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሶማሌ ክልል የመምህራን ቅሬታ

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 14 2013

በሶማሌ ክልል የሚገኙ መምህራን መንግሥት በሁለተኛ ዙር ሊከፍለን የሚገባው የሥራ ምዘናና ደረጃ አሰጣጥ ስርዓት ክፍያ (JEG) ካለፈው ሐምሌ ወር ጀምሮ አልተከፈልንም ሲሉ ቅሬታ አቅርበዋል። የክልሉ ትምህርት ቢሮ ጥያቄው አግባብ መሆኑን ገለልፆ በቀጣዩ በጀት ዓመት ሐምሌ ወር ላይ ለመክፈል ዕቅድ መያዙን ዐስታውቋል።

https://p.dw.com/p/3sRBb
Karte Sodo Ethiopia ENG

«ካለፈው ሐምሌ ወር ጀምሮ አልተከፈልንም »

በሶማሌ ክልል የሚገኙ መምህራን መንግሥት በሁለተኛ ዙር ሊከፍለን የሚገባው የሥራ ምዘናና ደረጃ አሰጣጥ ስርዓት ክፍያ (JEG) ካለፈው ሐምሌ ወር ጀምሮ አልተከፈልንም ሲሉ ቅሬታ አቅርበዋል፡፡ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ጥያቄው አግባብ መሆኑን ገለልፆ በቀጣዩ በጀት ዓመት ሐምሌ ወር ላይ ለመክፈል ዕቅድ መያዙን ዐስታውቋል፡፡

በሀገሪቱ በሚፈገኙ የመንግስት ተቋማት ተግባራዊ እየሆነ የሚገኘው የስራ ምዘናና ደረጃ አሰጣጥ ስርዓት (JEG) ጋር ተያይዞ ለመንግስት ሰራተኞች የሚከፈለው ሁለተኛ ዙር ክፍያ መከፈል ከነበረበት ካለፈው ሐምሌ ጀምሮ አልተከፈለንም ሲሉ በሶማሌ ክልል የሚገኙ መምህራን ለዶይቸ ቬለ (DW) ቅሬታ አቅርበዋል።

ከቅሬታ አቅራቢዎቹ መካከል አንዱ በሰጡት አስተያየት በሚሰሩበት አካባቢ ያለው የኑሮ ውድነት በተጨማሪ ማግኘት የሚገባቸው ክፍያ አለመስተካከል ችግር መፍጠሩን አስረድተዋል። የክልሉ መምህራን ማህበር ተወካይ በበኩላቸው በመምህራኑ የቀረበው ቅሬታ አግባብ መሆኑን ገልፀው ከክልሉ ጋር ሲነጋገሩ መቆየታቸውን ገልፀዋል።

የሶማሌ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ መሀመድ ፋታህ በበኩላቸው በመምህራኑ የተነሳው ቅሬታ ትክክለለኛ ነው ክልሉ በመጪው ሓምሌ ወር ያልተከፈለውን ክፍያ ለመክፈል ዕቅድ ማድረጉን ለDW በስልክ ተናግረዋል። በዚህም መግባባት ላይ ደርሰናል ባይ ናቸው።  ከአራት መቶ ሚልየን ብር በላይ ወጪን ይጠይቃል የተባለው የስራ ምዘናና ደረጃ አሰጣጥ ስርዓት ክፍያ ለክልሉ መምህራን ሊከፈል ያልቻለው በክልሉ ለዚህ ተብሎ የተያዘ በጀት ባለመኖሩ መሆኑ ተገልፃል።

መሳይ ተክሉ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
እሸቴ በቀለ