አምነስቲ፤ በሶማሌ ክልል ጉዳይ ፌደራል መንግሥት ባለሥልጣናት ሁሉ ይፈተሹ
ማክሰኞ፣ ነሐሴ 22 2010ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ የፌደራል መንግሥት ባለሥልጣናት ትናንት በታሰሩት በቀድሞዉ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ርዕሠ-መስተዳድር በአብዲ መሐመድ ዑመር ላይ የሚመሠርቱት ክስ እና የፍርድ ሒደት ግልፅ፤ ሚዛናዊ እና ከአድሎ የፀዳ እንዲሆን ሁዩማን ራይትስ ዋች ጠየቀ። አምነስቲ ኢንተርናሽናል በበኩሉ በቁጥጥር ሥር ከዋሉት ከቀድሞዉ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ርዕሠ-መስተዳድር እና ከቅርብ ተባባሪዎቻቸዉ በተጨማሪ የክልሉን ባለሥልጣናት የደገፉ፤ ልዩ ፖሊስ የሚባለዉን ኃይል ያደራጁ፤ ያስታጠቁ እና የሰብአዊ መብት ጥሰቱን ለረጅም ጊዜ በቸልታ ያለፉ የፌደራል መንግሥት ባለሥልጣናት እና ሌሎች አካላትም ሊጠየቁ ይገባል ብሏል። የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የምሥራቅ አፍሪቃ የሰብአዊ መብት አጥኚ አቶ ፍሰኃ ተክሌ ለዶይቸ ቬለ እንደነገሩት እንደ ጎርጎሪያኑ አቆጣጠር ከ2008 ጀምሮ የሰብአዊ መብት ጥሰት ሲፈፀም የፌደራል መንግሥቱ የሲቭል እና የፀጥታ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ዝምታን መምረጣቸዉ የተባባሪነት ሚና እንደነበራቸዉ አመልካች ነዉ። አቶ ፍስሃን ተክሌን ነጋሽ መሐመድ አነጋግሮአቸዋል።
ነጋሽ መሐመድ
አዜብ ታደሰ
አርያም ተክሌ