1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያዉያኑ ጠቅላይ ሚኒስትራቸዉን ለማግኘት ታድመዋል

ረቡዕ፣ ጥቅምት 21 2011

ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ በጀርመን ፍራንክፈርት ከተለያዩ የአውሮጳ ሀገራት ከተውጣጡ ኢትዮጵያውያን ጋር የሚያደርጉት ውይይት በሃይማኖት አባቶች ፀሎት ጀምሮአል። የ«DW» የቴሌቪዥን፣ የራድዮና የማኅበራዊ ሚድያ ጋዜጠኞች በቦታዉ ላይ በመገነኘት በፌስቡክ የቀጥታ ቪድዮችን፣ ፎቶግራፎችን እና ዝርዝር ጉዳዮችን የያዙ መረጃዎችን ማድረሳቸዉን ጀምረዋል።

https://p.dw.com/p/37Qwp
Frankfurt Ministerpräsident Äthiopien Abiy Ahmed in Commerzbank-Arena
ምስል DW/T. Waldyes

በፍራንክፉርት «ኮሜርስ አሬና» በተባለዉ ስቴዲየም ከጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ጋር ለመወያየት በተዘጋጀዉ መድረክ ለመገኘት ኢትዮጵያዉያንና እና ትዉልድ ኢትዮጵያዊያን ከተለያዩ አዉሮጳ ሃገራት እየተመሙ ነዉ። ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ እንደሚጀምር በተነገረዉ ዝግጅት ላይ ለመገኘት ስቴዲዮሙ ቀድመዉ የደረሱም ስቴድዮሙ ዉስጥ መግባት ጀምረዋል። በፍራንክፈርት ኮሜርዝ ባንክ አሬና ስቴድየም ቀድመው የተገኙ ኢትዮጵያውያን የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድን ስም እየጠሩ ድጋፋቸውን እየገለፁ ነዉ ። በዛሬው የፍራንክፈርት ዝግጅት ትርዒት የሚያቀርቡ አዳጊ የሰርከስ ባለሙያዎች የመጨረሻ ልምምዳቸውን እያደረጉም ነው። በስቴዲዮሙ በሙዚቃ መሳሪያ የተቀነባበሩ የኢትዮጵያ ሙዚቃዎች ለታዳሚያኑ እየቀረበ ይገኛል። ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ጋር ለመወያየት በስቴድየም የተገኙ ታዳሚያን በሀገርኛ ሙዚቃዎች እየተዝናኑ ነው። ትልቁ የኮሜርዝ ባንክ አሬና ስታዲየም የ «DW» ጋዜጠኞች ዘገባዎችን በቀጥታ በማሰራጨት ላይ ይገኛሉ።

Frankfurt Ministerpräsident Äthiopien Abiy Ahmed  in  Commerzbank-Arena
ምስል DW/Tesfalem Waldyes


አዜብ ታደሰ