1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኦክስጂን ማምረቻ በሶማሌ ክልል

ዓርብ፣ ሚያዝያ 29 2013

ማዕከሉ በኮቪድ 19 የታመሙ ሰዎችን ለመርዳት ያጋጥም ለነበረው የኦክስጅን እጥረት መፍትሄ ይሰጣል ተብሏል፡፡የሶማሌ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዩሱፍ መሀመድ በተለይ ለዶቸቬለ እንዳሉት ማዕከሉ በቀን 200 የኦክስጅን ሲሊንደሮችን መሙላት ይችላል።ምርቱ ከሶማሌ ክልል አልፎ ለሐረሪ ክልልና ለድሬዳዋ ከተማ መስተዳድር እንደሚደርስ ኃላፊዉ አስታዉቀዋል።

https://p.dw.com/p/3t6VC
Äthiopien Sauerstoff-Aufbereitung
ምስል Mesay Tekilu/DW

ኦክስጂን ማምረቻ በሶማሌ ክልል

የሶማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መስተዳድር ለምስራቅ ኢትዮጵያ አካባቢዎች የሚውል ኦክስጅን ማምረቻና ማከፋፋያ  ማዕከል ማቋቋሙን አስታወቀ፡፡ ማዕከሉ በኮቪድ 19 የታመሙ ሰዎችን ለመርዳት ያጋጥም ለነበረው የኦክስጅን እጥረት መፍትሄ ይሰጣል ተብሏል፡፡የሶማሌ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዩሱፍ መሀመድ በተለይ ለዶቸ ቬለ እንደነገሩት ማዕከሉ በቀን ሁለት መቶ የኦክስጅን ሲሊንደሮችን መሙላት ይችላል።ምርቱ ከሶማሌ ክልል አልፎ ለሐረሪ ክልልና ለድሬዳዋ ከተማ መስተዳድር እንደሚደርስ ኃላፊዉ አስታዉቀዋል።የድሬዳዋዉ ወኪላችን መሳይ ተክሉ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል። 

መሳይ መኮንን

ኂሩት መለሰ

አዜብ ታደሰ