1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች: ወጣቶች በማህበረሰቡ ዘንድ እንዴት ይታያሉ ?

ዓርብ፣ ነሐሴ 17 2016

ወጣት አቤጌል እሸቱ እና ማህሌት ስንታየሁ የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች የ12 ክፍል ተማሪዎች ናቸው ፡፡ ከዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች ዝግጅት ጋር ቆይታ ያደረጉት አቤጌል እና ማህሌት ማህበረሰቡ በወጣቶቸች ላይ አዎንታዊም አሉታዊም አተያይ እንዳለው ይናገራሉ ፡፡ ይሁንና አሉታዊው ይጎላል ባይ ናቸው።

https://p.dw.com/p/4johu
Äthiopien Interview Jugend Hawasa Jugendliche
ምስል Shewangizaw Wegayoh/DW

ወጣቶች በማህበረሰቡ ዘንድ እንዴት ይታያሉ ?

አሁን ላይ ማህበረሰቡ በወጣቶች ላይ ያለው እምነትእ የላላ መምጣቱን መታዘቧን የጠቀሰችው አቤጌል “ በተለይ ወጣቱ ለሥራ ያለው ፍላጎት ዝቅተኛ ነው ፡፡ በትዕግሥት ጥረቶችን ከማድረግ ይልቅ በአጭር ጊዜ የተሻለ ነገር ለማግኘት መሻት ይስተዋልበታል ፡፡ በተጨማሪም ሁሉም ባይሆንም በአብዛኛው የሱሶች ተጠቂ ሆነው የሚገኙ አሉ፡፡ በዚህም የተነሳ አብዛኛው የማህበረሰብ ከፍል በወጣቶችን ላይ እምነት እንዲያጣ እያደረገው ይገኛል  “ ብላለች
ወጣት ማህሌት በበኩሏ አሁን ያለነው ትውልዶች እድለኞች ነን ትላለች  ፡፡ ከቀደምት ትውልዶች ጋር ሲነጻጸር መደበኛ ትምህርት ለመማር የተሻለ እድል እንዳለው የጠቀሰችው ማህሌት “ በተለይ ለህይወቱና ለሥራው የሚያስፈልጉትን መረጃዎች በቀላሉ ማግኘት ይችላል ፡፡ ነገር ግን የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎችን እንዴት መጠቀም እንዳለበት ካለማወቅ በስተቀር ሁሉ ነገር በእጃችን ላይ ይገኛል “ ብላለች ፡፡
ያምሆኖ ወጣቶችን በተመለከተ በማህበረሰቡ ውስጥ በአዎንታዊም በአሉታዊም የሚነሱ አመለካከቶች እንደሚታዩ ወጣት ማህሌት ገልጻለች ፡፡ በጎ ባልሆነ መልኩ የሚነሱ አመለካከቶች መኖራቸው የሚታዩና አውነትነት ያላቸው መሆኑን የምትናገረው ማህሌት “ በተለይም በትምህርት ቤቶች አካባቢ የሚታዩ የመጠጥ እና የጫት ቤቶች ለወጣቶች ባህሪ መበላሸት ምክንያት እየሆኑ ይገኛሉ  ፡፡ ተማሪው ከትምህርት ሲወጣ ያንን በማየት በቀላሉ ሊሳብ ይችላል ፡፡ ይህም ቀጣይ ህይወቱን በማበላሸት በማህበረሰቡ ውስጥ በጎ ያልሆነ አተያየት እንዲፈጠር ያደርጋል “ ብላለች ፡፡

ወጣት አቤጌል እሸቱ እና ማህሌት ስንታየሁ ከአወያይዋ ሊሻን ዳኜ ጋር ቁጭ ብለው
ወጣት አቤጌል እሸቱ እና ማህሌት ስንታየሁ የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች የ12 ክፍል ተማሪዎች ናቸውምስል Shewangizaw Wegayoh/DW

 ወጣቶች ከታላላቆቻችን ለመማር መዘጋጀት አለብን የሚሉት አቤጌል እና ማህሌት  “ ወጣቱ ለራሱ ጊዜ በመስጠትና ከቤተሰቡም ሆነ ከማህበረሰቡ አባላት ጋር በመግባባት መልካም ስብዕና ለመላበስ መጣር ይኖርበታል ፡፡ ወላጆችና ማህበረሰቡ ከእኛ ብዙ ነገር ይጠብቃሉ ፡፡ በመሆኑም  ማህበረሰቡ በወጣቶች ላይ የሚሰጣቸውን በጎ አስተያየቶች ማጠናከር እና አሉታዊ ምልከታዎችን ደግሞ ማስተካከልና ማረም ይጠበቅብናል “ ብለዋል ፡፡

#ዝምታሰባሪአዳጊሴቶች #GirlzOffMute
 

ሊሻን ዳኜ/ሸዋንግዛው ወጋየሁ  
ልደት አበበ