1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የነዳጅ መወደድ እና ተግዳሮቱ

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 5 2014

መንግሥት የነዳጅ ምርቶችን ለመደጎም በየወሩ በአማካይ 10 ቢሊዮን ብር ወጪ እያደረገ ለረጅም ዓመታት መቆየቱ ለከፍተኛ የዕዳ ክምችት እንዳጋለጠው በመግለጽ ድጎማውን ደረጃ በደረጃ ማንሳት ጀንሯል። ድጎማውን ማስቀጠል አዳጋች ሆኖብኛል ያለው መንግሥት ካለፈው ሳምንትጀምሮ ከፍተኛ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ አድርጓል።

https://p.dw.com/p/4E18b
Äthiopien | Tanken | Addis Abeba
ምስል S. Muchie/DW

ሸቆጦች ዋጋቸው እጥፍና ከእጥፍ በላይ ጨምሯል


መንግሥት የነዳጅ ምርቶችን ለመደጎም በየወሩ በአማካይ 10 ቢሊዮን ብር ወጪ እያደረገ ለረጅም ዓመታት መቆየቱ ለከፍተኛ የዕዳ ክምችት እንዳጋለጠው በመግለጽ ድጎማውን ደረጃ በደረጃ ማንሳት ጀንሯል። ድጎማውን ማስቀጠል አዳጋች ሆኖብኛል ያለው መንግሥት ካለፈው ሳምንትጀምሮ  ከፍተኛ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ አድርጓል።
"በኢትዮጵያ ውስጥ ለተከሰተው ማንኛውም የምጣኔ ሀብት ቀውስ የመጀመሪያው ተጠያቂ መንግስት ነው የሚሉት የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ዶክተር ጉቱ ዋሱ  በአገሪቱ ውስጥ እየተንሰራፋ የመጣውን ሥርዓት አልበኝነት እና የሰላምና መረጋጋት መጥፋቱን መንግሥት ማስትካከል አለመቻሉ ከነዳጅ ድጎማው መነሳት ጋር ተዳምሮ ኑሮን ፈታኝ ያደርገዋል ይላሉ።
የነዳጅ ድጎማው የመነሳት ውሳኔ አደገኛ እና የተሳሳተ የምጣኔ ሀብት እርምጃ ነው ብለዋል። ለድንገተኛ እና ምክንያታዊ ላልሆኑ የዘፈቀደ የሸቀጦች የዋጋ ጭማሪ ተጋላጭ የሆነው የኢትዮጵያ ገበያ ከፍተኛ ደረጃ ደርሷል በሚባለው የኑሮ ውድነት ላይ ይህ የነዳጅ ድጎማ መነሳት ሊያስከትል የሚችለውን ተጽእኖ ለመዳሰስ ሞክረናል። 
በክረምት ወቅት ፣ ብርድ በሚያይልበት ጊዜ ፣ በከተማው ከነ ትኩስ እንፋሎቱ በትንሽ ጋሪ እየተዞረ የሚሸጥ ቅቅል እና የተጠበሰ የበቆሎ እሸት የተለምደ የብርድ ጊዜ ምግብ ነው። ይሄው የበቆሎ እሸት እንደወትሮው በአነስተኛ ገንዘብ የሚቀመስ አልሆን እያለ የመጣ ይመስላል። አንድ ዛላ ቆረቆንዳ በቆሎ ተጠብሶም በ20 ፣ ተቀቅሎ ደግሞ በ25 ብር እየተሸጠ ይገኛልና። መንግሥት የነዳጅ ምርቶችን ለመደጎም በየወሩ በአማካይ 10 ቢሊዮን ብር ወጪ እያደረገ ለረጅም ዓመታት መቆየቱንና በአሁኑ ወቅት 147 ቢሊዮን ብር ገደማ ለነዳጅ ድጎማ ያዋለው ገንዘብ ዕዳ እንዳለበት ተገልጿል።
ይህንንም ማስቀጠል አዳጋች ስለሆነበት ድጎማውን ቀስ በቀስ ለማንሳት ውሳኔ አሳልፎ ባለፈው ሳምንት ከፍተኛ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ተደርጓል። የዋጋ ጭማሪው ተጽእኖ ገና በጉልህ መታየት ባይጀምርም 52 ብር በገባው የአንድ ዶላር አቻ የብር ምንዛሪ ግብይት ከውጭ የሚገቡ ምርቶች ዋጋ መናር እያሳየ ይገኛል።
የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ዶክተር ጉቱ ዋሱ ይህን የነዳጅ ድጎማ የመነሳት ውሳኔ አደገኛ እርምጃ ይሉታል። ከሦስት እና አራት ወራት በፊት ባንኮች ለደንበኞቻቸው ብድር ፈቅደውላቸው ይደረግ በነበረ ግብይት ከአዲስ አበባ ጫፍና ጫፍ በታነፁ የጋራ መኖሪያ ቤቶች የባለ ሁለት መኝታ 70 ካሬ የጋራ መኖሪያ ቤት እስከ 2.7 ሚሊዮን ብር ሲሸጡ ነበር። አሁን ይህን መሰሉ ቤት እስከ 3.5 ሚሊዮን ብር ይሸጣል የሚለው የቤት ግብይት አሳላጭ ደላላ የኑሮው ውድነት የፈጠረውን የገንዘብ የመግዛት አቅም ማነስ በቁጥር አስደግፎ ለ DW ተናግሯል።
የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ዶክተር ጉቱ ዋሱ የዚህ ወር የዋጋ ንረት ካለፈው ዓመት ለንጽፃሬ ሲቀርብ ሸቆጦች ዋጋቸው እጥፍና ከእጥፍ በላይ ጨምሯል። አንዱ የዚህ የዋጋ ጭማሪ ምክንያት ደግሜ የነዳጅ ዋጋ መጨመር ነው ይላሉ።
እናም አሁን በዚህ የኑሮ ውድነት ምክንያት ከ30 ሚሊዮን ሕዝብ በላይ ከነበረበት የድህነት ወለል በላይ ወደ ከድህነት ወለል በታች ወርዷል ብለዋል። ስለዚህም የመንግሥት ውሳኔ ተገቢነትና ምክንያታዊነት ይጎድለዋል ሲሉ ይከራከራሉ። አሁን የተነሳው የተወሰነው መጠን የነዳጅ ዋጋ ድጎማ የተሽከርካሪዎች ግብይት ላይ ተጽእኖ ስለማሳረፍ አለማሳረፉ በከተማው ካሉ ልዩ ልዩ አውቶሞቢል ሻጮች አንደኛውን ጠይቀናቸዋል።
"ምንም አዲስ ነገር የለም " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። ቀጣዩን ጊዜ መጠበቅ እንደሚበጅ በመጠቆም። "በኢትዮጵያ ውስጥ ለተከሰተው ማንኛውም የምጣኔ ሀብት ቀውስ የመጀመሪያው ተጠያቂ መንግስት ነው" የሚሉት የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ዶክተር ጉቱ " በአገሪቱ ውስጥ እየተንሰራፋ የመጣውን ሥርዓት አልበኝነት እና የሰላምና መረጋጋት መጥፋቱን መንግሥት ማስትካከል ይችል ነበር" በማለት ይህ አለመደረጉ መሰረታዊ አባባሽ ችግሮች መሆናቸውንና ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባው ላይ አለማተኮርንም ሊስተካክል የሚገባ እንደነበር ይዘረዝራሉ።
የነዳጅ ድጎማው መነሳት በአብዛኛው ከትራንስፖርት አገልግሎት ጋር ብቻ ሲያያዝ ይስተዋላል። ይሁንና የኤሌክትሪክ አቅርቦት በስፋት በሌለባቸው ቦታዎችና በኃይል መቆራረጥ ምክንያት በጀነሬተሮች ለመስራት አማራጭ የሚጠቀሙ ሰፊ የሥራ መስኮችንም ጭማሩው ማስጨነቁ አይቀርም።
ከሕዝብ ትራንስፖርት ባልተናነሰ ከፍተኛ ግልጋሎት ሰጪዎቹ የጭነት ተሽከርካሪዎች የድጎማው ዘላቂ ተጠቃሚ አለመሆናቸውም ኑሮን የባሰ አባባሽ መሆኑ እንደማይቀር ይታመናል። የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ በቅርቡ የተደረገውን የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ተከትሎ የከተማ ውስጥ የመጓጓዣ ሒሳብ ክለሳ ስለማድረግ አለማድረጉና ተያያዥ ጉዳዮች የፊታችን ረቡዕ መግለጫ እንደሚሰጥ ገልጾልናል።

Äthiopien | Warteschlagne vor Tankstelle in Dire Dawa
ምስል Messay Teklu/DW
Äthiopien | Warteschlagne vor Tankstelle in Dire Dawa
ምስል Messay Teklu/DW


ሰለሞን ሙጬ


አዜብ ታደሰ 
እሸቴ በቀለ