1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ኅብረተ ሰብሰሜን አሜሪካ

አዲስ ዓመት በዋሽንግተን ዲሲ

ማክሰኞ፣ መስከረም 1 2016

በአሜሪካ አዲስ ዓመትን የሚያከብሩ ኢትዮጵያውያን የዘንድሮው አዲስ ዓመት ኢትዮጵያ ውስጥ ሰላም ፍቅርና ደህንነት የሚሰፍንበት እንዲሆን ምኞታቸውን ገልጸዋል። ዓመት በአሉን ምንም ሳይጎልባቸው የሚያከብሩት ቢሆንም፣ ሃሴትና ደስት እንደራቃቸው፣ መንፈሳቸው በሃገር ቤት ውስጥ በነገሰው የሰላምና የደህንነት ችግር እንደታወከ ነው የገለጹት ።

https://p.dw.com/p/4WFnU
ኢትዮጵያውያን በዋሽንግተን ዲሲ
አሌክሳንድሪያ ቨርጂንያ በምትገኘው የቅድስት አርሴማ፣ ወቅዱስ ቂርቆስ ፣ወቅዱስ ዑራኤል ፣ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን አዲሱን ዓመት ሲያከብሩ።ምስል Abebe Feleke/DW

የአዲስ ዓመት አከባበር በዋሽንግተን ዲሲ

በአሜሪካ አዲስ ዓመትን የሚያከብሩ ኢትዮጵያውያን የዘንድሮው አዲስ ዓመት ኢትይጵያ ውስጥ ሰላም ፍቅርና ደህንነት የሚሰፍንበት እንዲሆን ምኞታቸውን ገልጸዋል። ዓመት በአሉን ምንም ሳይጎልባቸው የሚያከብሩት ቢሆንም፣ ሃሴትና ደስት እንደራቃቸው፣ መንፈሳቸው በሀገር ቤት ውስጥ በነገሰው የሰላምና የደህንነት ችግር እንደታወከ ነው የገለጹት ።

የአዲሱ አመት ገበያ እንደወትሮው ደምቋል። ቨርጂኒያ የሚገኘው የመርካቶ ገበያ ባለቤት ው/ሮ አበባ ገብረመስቀል ሁሉም ነገር የተሟላ ቢሆንም፣ የሁሉም ሰው ፍላጎት ኢትዮጵያ ውስጥ ሰላም ሰፍኖ ማየት እንደሆነ ገልጸዋል።

አዲሱን ዓመት አሌክሳንድሪያ ቨርጂንያ በምትገኘው የቅድስት አርሴማ፣ ወቅዱስ ቂርቆስ ፣ወቅዱስ ዑራኤል ፣ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ተሰባስበው ያከበሩት ኢትዮጵያውያን ስሜት ተመሳሳይ ነው። ከታዳሚወቹ አንዱ አቶ አበበ ካሳ በአሉን ከኢትዮጵያ ባልተናነሰና፣ ልጆች ባህላቸውን እና ማንነታቸውን እንዲያውቁ በሚያደርግ መልኩ እየተከበረ መሆኑን ገልጿል። እዚሁ አሜሪካ ውስጥ የተወለደው ታዳጊ አማኑኤል መኮንንም ምኞቱ ኢትዮጵያ ውስጥ ሰላም ሰፍኖ ማየት ነው

ኢትዮጵያውያን በቨርጂኒያ በዓሉን ሲያከብሩ
ኢትዮጵያውያን የዘንድሮው አዲስ ዓመት ኢትይጵያ ውስጥ ሰላም ፍቅርና ደህንነት የሚሰፍንበት እንዲሆን ምኞታቸውን ገልጸዋል። ምስል Abebe Feleke/DW

በዚሁ የማኅበረሰብ ዝግጅት ላይ የታደመችው ወ/ሮ ራሄል ተወልደም በበኩሏ አዲሱን አመት ልክ እንደ ኢትዮጵያ አድርገው ከቤተሰብ ጋ እንደሚያከብሩት ገልጻ፣ የዘንድሮው ዓመት በአል ግን ከሁሉም በላይ ሰላምና ደህንነት የሚፈለግበት እንደሆነ ተናግራለች ። ሌላዋ ታዳሚ ኩሪ የዘንድሮው ዓመት በዓል እንደወትሮ ሃሴትና ደስታ የሞላበት እንዳልሆነ ገልጻለች ።

ዋዜማው ምሽት ላይ ወዳጅ ጓደኞቻቸውን ሲያስተናግዱ ያመሹት አቶ ሰለሞን ሽመልስና ባለቤቱ ማኅሌትም ከእንግዶቻቸው ጋ አዲሱን አመት ከተስፋና ከምኞት ጋ አክብረውታል። የሚበላው የሚጠጣው አልጎደለም ያሉት አቶ ሰለሞን፣ ሁሉም ሰው በአካል እዚህ ቢሆንም በመንፈስ ኢትዮጵያ ነው ብለዋል። በምሽቱ የታደሙት ጓደኛሞች ከመዝናናትና ከመጫወት አልፈው ሃገር ቤት በተለይ በት/ቤቶችና በተማሪወች ላይ ያተኮረ የበጎ አድራጎት ተግባራትን ይከውናሉ። እዚሁ ቤት ውስጥ በአሉን ለማክበር ከታደሙት ወስጥ፣ አሜሪካ ከሰላሳ ስድስት ዓመታት በላይ የኖሩት አቶ ዮሐንስ ደምሴም የ2016 አዲስ አመት ምኞታቸው የሃገራችንን ሰላምና ፍቅር ማየት ነው።

ቨርጂኒያ ዩናይትድ ስቴትስ
አሌክሳንድሪያ ቨርጂንያ በምትገኘው የቅድስት አርሴማ፣ ወቅዱስ ቂርቆስ ፣ወቅዱስ ዑራኤል ፣ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን አዲሱን ዓመት ሲያከብሩ።ምስል Abebe Feleke/DW

አበበ ፈለቀ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ታምራት ዲንሳ