የኤርትራ ስደተኞች በአፋር
ሐሙስ፣ ሚያዝያ 15 2012ማስታወቂያ
አፋር መስተዳድር በርሀሌ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ የሰፈሩ የኤርትራ ስደተኞች በየወሩ ይሰጣቸዉ የነበረዉ የምግብ ርዳታ መቋረጡን አስታወቁ።ስደተኞቹና ለስደተኞቹ መብት እንከራከራለን የሚሉ ወገኖች እንደሚሉት ለስደተኞቹ ይሰጥ የነበረዉ የምግብ ርዳታዉ ከተቋረጠ ሁለት ወር አለፈዉ።አዳዲስ የሚመጡ ስደተኞች መመዝገባቸዉም ቆሟል።የስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች ጉዳዮች ዔጀንሲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ያሲን አልዬ ግን የምግብ እደላም ሆነ አዳዲስ የሚመጡ ስደተኞችን መመዝገቡ አልተቋረጠም ባይ ናቸዉ።
መሳይ ተክሉ
ነጋሽ መሐመድ
እሸቴ በቀለ