Tesfalem Waldyes Eragoሰኞ፣ ነሐሴ 7 2010በዕለቱ የዜና መፅሄት ትላንት በሻሸመኔ ከተማ ሰዎች ስለሞቱበት መርኃ ግብር የኦሮሚያ ክልል የሰጠውን ምላሽ ይዘናል። በኢትዮጵያ የብሔራዊ መግባባት እና እርቀ ሰላም ጉባኤ እያዘጋጁ ያሉት የተቃዋሚ ፓርቲዎች የሰጡትን ጋዜጣዊ መግለጫም እንመለከታለን። ትላንት ወደ ኢትዮጵያ ስለገባው የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻነት ግንባር (ኦብነግ) ከፍተኛ የልዑካን ቡድን የተጠናቀረ ዘገባም አለን። የፈረንሳይ ፖሊስ ስደተኞችን በሚያግዙ በጎ ፍቃደኞች ላይ ይፈጽማል ስለሚባለው ጥቃት የሚዳስስ ዘገባም በዜና መጽሔታችን ተካትቷል።