1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዩኤስ ባለሥልጣን የአፍሪቃ ጉብኝት

ቅዳሜ፣ ጥቅምት 18 2010

በተመድ የዩኤስ አሜሪካ አምባሳደር ኒኪ ሄይሊ በዚህ ሳምንት በሶስት የአፍሪቃ ሃገራት ጉብኝት አድርገዋል። ሄይሊ በኢትዮጵያ ፣ በደቡብ ሱዳን ያደረጉት ጉብኝታቸው ፣ ዩኤስ አሜሪካ ከአፍሪቃ ጋር ያላትን ግንኙነት እና የተመድ በአህጉሩ የሚያካሂዳቸውን የሰላም ማስከበሪያ ተልዕኮዎች በቅርብ የመመልከት ዓላማ ነበረው።

https://p.dw.com/p/2mg4u
DRK US-Botschaftlerin bei der UN Nikki Haley in N'Djili Flughafen in Kinshasa
ምስል Reuters/R. Carrubba

አምባሳደር ኒኪ ሄይሊ በአፍሪቃ

ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ስልጣን ከያዙ ካለፉት አስር ወራት ወዲህ አንድ ከፍተኛ የዩኤስ አሜሪካ ባለስልጣን ወደ አፍሪቃ ሲሄድ ኒኪ ሄይሊ የመጀመሪያዋ ናቸው። ይኸው ጉዟቸው ፕሬዚደንት ትራምፕ አሜሪካ ትቅደም የሚለውን መርሀቸውን ማጉላት በያዙበት ባሁኑ ጊዜ፣ ዩኤስ አሜሪካ በአፍሪቃም የመሪነቱን ቦታ ለመያዝ ያላትን ፍላጎት ግልጽ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል። 

ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ስለ አሜሪካ በመጀመሪያ ሲናገሩ ብዙ ጊዜ ዓለም አቀፍ ውሎችን እና ድርጅቶችን ለመቃወሚያ ነው። እንደ ትራምፕ አባባል፣ እነዚህ ውሎችና ድርጅቶች የአሜሪካን ጥቅም ጥሩ እንዳልሆኑ፣ የስራ ቦታ የሚያጠፉ እና ተጨማሪ ገንዘብ የሚያስወጡ እና ዩኤስ አሜሪካን የማታስተማምን ቦታ የሚያደርጉ ናቸው፣ ይሁን እንጂ፣  ይህ በምርጫ ዘመቻ ወቅት ያሰሙት የነበረውና አሁንም የቀጠሉት አነጋገር በውጭ ፖለቲካው መድረክ ላይ እንዴት ተግባራዊ ማድረግ መቻሉ ግን ዛሬ ከዘጠን ወራት በኋላም ግልጽ አልሆነም። ታዛቢዎች እንደሚሉት፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ የፊናንሱ ድጋፍ  እና የፖለቲካው ታታሪነት ትብብር የሚቀንስበት ሁኔታ ለአሜሪካ ጠቃሚ አይደለም። የትራምፕን ቀል በአጽናፋዊ ትስስር ከሚገኝ ዓለም የውጭ ፖለቲካ መድረክ ላይ ገቢራዊ የማድረጉ ሙከራ አሁን በኒኪ ሄይሊ የአፍሪቃ ጉዞ ወቅት የሚታይ ይሆናል።
የ45 ዓመቷ ሄይሊ በጉዟቸው ወቅት ከርዕሳነ ብሔር እና ከመራሕያነ መንግሥታት ጋር ከሚያደርጉት ግንኙነት በተጨማሪ በደቡብ ሱዳን እና በዴሞክራቲክ ኮንጎ ሬፓብሊክ የተሰማሩትን የተመድ ሰላም አስከባሪ ተልዕኮዎች ስራ ትኩረት አግኝተዋል። በኢትዮጵያ በጋምቤላ ያለውን በብዛት የደቡብ ሱዳን ስደተኖች የሚገኙበትን የመጠለያ ጣቢያ የጎበኙት ሄይሊ ሀገራቸው የደቡብ ሱዳንን ህዝብ እንደማትረሳ ገልጸዋል።
ሄይሊ በጁባ ከደቡብ ሱዳን ፕሬዚደንት ሳልቫ ኪር ጋር ከተወያዩ በኋላ በሰጡት መግለጫም የሀገሪቱ ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑን ገልጸው፣ ዩኤስ አሜሪካ በደቡብ ሱዳን ፕሬዚደንት ላይ አመኔታ እንደሌላት አስታውቀዋል። 

USA Donald Trump spricht vor afrikanischen Staatschefs
ምስል Getty Images/AFP/B. Smialowski

ሄይሊ በደቡብ ሱዳንና ኮንጎ የተጀመሩት ተልዕኮዎቹ የተቀመጠላቸውን ዓላማ ከግብ ያላደረሱ፣ ግዙፍ ወጪ ብቻ የፈጁ ናቸው ሲሉ በተደጋጋሚ በመውቀስ፣ የተመድ ሰላም ም ተልዕኮዎች ቅድሚያ ተሰጥቷቸው ተሀድሶ እንዲደረግባቸው ሀሳብ ሲያቀርቡ ተሰምተዋል። ከዚህ ባለፈም የሰላም ጥረቶችን በሚያሰናክሉ በመሪዎቹ ላይ ግፊት እንዲያርፍም አሳስበዋል። 
የአሜሪካውያን የብሩኪንግስ የፖለቲካ ጥናት ተቋም የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ተንታኝ ሀዲ አስተያየት ግን በዚሁ ረገድ ትልቅ ለውጥ ይኖራል ብለው አያስቡም። 
« የዩኤስ አሜሪካ መንግሥት በሚሰጠው ድጋፍ ላይ ጉልህ ቅነሳ የማድረግ ዓላማ እያለው ይህን ዓይነት ጉዞ ያዘጋጃል ብዬ አላስብም። »
በዚህ ፈንታ አሜሪካዊቷ ባለስልጣን በጉብኝታቸው ወቅት መረጃዎችን ለመሰብሰብ ነው የሞከሩት። 
«ፕሬዚደንት ትራምፕም ሆኑ ኒኪ ሄይሊ በአፍሪቃም ሆነ በነዚህ አስቸጋሪ እና ከባድ ጉዳዮች ላይ የመስራትም ተሞክሮ አላቸው ብዬ አላስብም። በቅርብ አብረዋቸው የሚሰሩት ጓዶቻቸውም ቢሆኑ እንዲሁ። እና አሁን እየተደረገ ያለው ወደቦታው በመሄድ ሁኔታዎችን የመመልከት እና የማጣራት ስራ ነው።»

Somalia Mogadischu | Hilfsgüter des WFP & USAID
ምስል DW/S. Petersmann

የኒሁ የትራምፕ ከፍተኛ ተወካይ የመጀመሪያ ረጅም የአፍሪቃ ጉዞ ብዙ ማነጋገር ይዟል፣ ምክንያቱም፣ አራቱ አሜሪካውያን ወታደሮች በኒዠር ከሞቱ  ከጥቂት ጊዜ በኋላ ነው የተደረገው። ወታደሮቹ በብዙ የአፍሪቃ ሀገራት ፀረ ሽብር ዘመቻ የሚያካሂደው የዩኤስ አሜሪካ የአፍሪካ እዝ፣ በምህጻሩ የአፍሪኮም አባላት ነበሩ። ይህ የዩኤስ አሜሪካን መንግሥት አዳጋች ሁኔታ ውስጥ እንደጣለው  በለንደን የስኩል ኦፍ ኦሪየንታል ኧንድ አፍሪካን ስታዲስ የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር ፊል ክላርክ ገልጸዋል።

«የዩኤስ አሜሪካ ልዩ ኃይላት አባላት ከሁለት ሳምንት በፊት በኒዠር መሞታቸው አፍሪኮም ከረጅም ጊዜ አንስቶ በአህጉሩ የሚያደርገው እንቅስቃሴ ምን ያህል ሰፊ መሆኑን አጋልጧል።  በነዚህ አፍሪቃውያት ሀገራት ውስጥ የዩኤስ አሜሪካ ጦር ኃይላት መሰማራታቸው ብዙ አሜሪካውያንን በጣም አስገርሟል ብዬ አስባለሁ።» አፍሪቃውያኑ አስተናጋጅ ሀገራት በፀጥታ ጥበቃው ጉዳይ ላይ ከዩኤስ አሜሪካ ግልጽ ምላሽ እንደሚጠብቁ ፊል ክላርክ ገልጸዋል። 

አፍሪኮም እንቅስቃሴው በግልጽ የማይታወቅ አካል ነው። ብዙ ሰዎች ከሚያስቡት በላይ በብዙ ሀገራት ውስጥ ይሰራል። አፍሪኮም በትክክል ምን እየሰራ መሆኑ ለሚገኝባቸው አፍሪቃውያት ሀገራት ራሳቸው ግልጽ አይደለም። እና አፍሪኮም ቢያንስ በፕሬዚደንት ትራምፕ አመራር ስር የዩኤስ አሜሪካ ፀጥታ እንቅስቃሴ ትኩረት ስለሚያገን ፣ የዚሁ እዝ ልዩ ኃይላት ምን እያደረጉ መሆናቸውን በተመለከተ ትልቅ ግልጽነት እንዲኖር፣ይህንኑ መረጃም ይፋ እንዲሆን እና ስራቸውን እንዴት እያከናወኑ መሆኑን የማወቅ ፍላጎት ይኖራል።

USA Ankunft der toten US-Soldaten aus dem Niger
ምስል picture alliance/AP Photo/L. Hiser/U.S. Army

አፍሪቃውያኑ መሪዎች ግን በፀጥታ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን ዩኤስ አሜሪካ በአፍሪቃ አኳያ የምትከተለው ፖሊሲ አቋም ምን መሆኑን ኒኪ ሄይሊ በግልጽ እንዲያሳውቁ ይፈልጋሉ።  ምክንያቱም፣  እስካሁን አፍሪቃ በአሜሪካውያን ባለስልጣናት የውጭ ፖሊሲ መግለጫዎች ላይ ሳትጠቀስ ነው የታለፈችው።  ማዕከላይ ለሚባሉ ዲፕሎማሲያዊ ስልጣኖችም ከብዙ ወራት ወዲህ ሰው አልተሾመላቸውም። ያም ቢሆን ግን፣ አንዳንድ አቅጣጫዎች መታየታቸውን ክላርክ ታዝበዋል።

በተለይ የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቅድሚያ ከሚሰጣቸው የሰብዓዊ ርዳታ፣ የሰብዓዊ መብት እና ዴሞክራሲ ጥያቄዎች ራሱን ያራቀበት በዚህ አንንጻር ትኩረቱን በዩኤስ አሜሪካ እና በአፍሪቃ መካከል አዲስ የንግድ ግንኙነት የሚፈጠርበትን መንገድ ለመክፈት ተጨማሪ ሙከራ እያደረገ ያለበትን ትልቅ ለውጥ እያየን ነው።  

ከዚህ ባለፈም የዩኤስ አሜሪካ አስተዳደር ለሀገሩ በአፍሪቃ የንግዱን ሁኔታ ለማመቻቸት ሲል በአፍሪቃውያኑ ላይ ግፊት ሊያሳርፍ ይችል ዬሆናል የሚል ስጋት መኖሩን ክላርክ ጠቁመዋል።
ትራምፕ ከሁለት ሳምንታት በፊት ብዙዎቹ ጓደኞቻቸው በአፍሪቃ በሚያደርጉት ታታሪነት ለመበልጸግ እንደሚፈልጉ ያሰሙት አስተያየት በአህጉሩ በጠቅላላ እንደ ማስጠንቀቂያ ደወል ነው ያቃጨለው። ይህ አባባላቸው ምናልባት አፍሪቃውያን መንግሥታት የንግዱን ማከላከያ እንዲያነሱ ለማስገደድ እና ለዩኤስ አሜሪካ የሚመች የንግድ ሁኔታ እንዲፈጥሩ የሚያስገደድ ሊሆን ይችላል የሚል ስሜት ፈጥሯል። ይሁን እንጂ፣ ለአፍሪቃ መንግሥታት ግን በገሀድ ምን ጥቅም ሊያስገኝ ይችላል የሚለውን ጥያቄ አልፎታል።  

የሄይሊ ጉዞ አሜሪካ መጀመሪያ የሚለው የትራምፕ አነጋገር ለዩኤስ አፍሪቃ ፖሊሲ ም የሚሰራ መሆን አለመሆኑን ወይም የትራምፕ መንግስት ትብብር ይከተል እንደሆን ይለያል ተብሎ ይጠበቃል።

አርያም ተክሌ
ማንተጋፍቶት ስለሺ