1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጆ ባይደንን መንግሥት የፈተነዉ የስደተኞች ፍልሰት

ሰኞ፣ ግንቦት 7 2015

ከኮቪድ 19 ጋር ተያይዞ የወጣው የስደተኞች እገዳ መነሳቱን ተከትሎ አሜሪካ በስተኞደተኞች ማዕበል ቀውስ ውስጥ ገብታለች። ችግሩ ከድንበር ከተሞች አልፎ ሌሎች ግዛቶችንም የተለያዩ ቀዉሶች ውስጥ እየጨመረ መሆኑ ተገልጿል። የጆ ባይደን አስተዳደርም ሆነ የህግ አውጪ አካላት ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችል የጋራ መግባባት ላይ አልደረሱም።

https://p.dw.com/p/4RN0E
USA Mexiko Migration Grenze Title 42
ምስል ALFREDO ESTRELLA/AFP

በትራምፕ ዘመን የወጣዉ ህግ 2 8 ሚሊዮን ፍልሰተኞችን ድንበር መልሶ ነበር


ፍልሰተኞችን ከድንበር ላይ ይዞ ወደመጡበት አገር የሚመልሰውና፣ በትረምፕ ዘመን የወጣው “አንቀፅ 42” የተባለዉ ደንብ ባለፈዉ ሳምንት ማብቃቱን ተከትሎ በርካታ ስደተኞች ከደቡብ አሜሪካ ሃገሮች ወደ ዩናይትድ ስቴትስ እየጎረፉ ነዉ። ይህ ፍልሰተኞችን ከድንበር የሚመልሰዉ ህግ በትራምፕ ዘመን 2 8 ሚሊዮን ፍልሰተኞችን ድንበር ላይ ይዞ ወደ ሃገራቸዉ መልሷል። ለትራምፕ አስተዳደር ከፍተኛ ራስ ምታት የሆነዉን የፍልሰተኞች ጎርፍ ለመግታት ፈጣን መፍትሄ እንዲያገኝ ይጠበቃል። ይሁንና ችግሩ ከድንበር ከተሞች አልፎ ሌሎች ግዛቶችንም ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፈተናዎች ውስጥ እየጨመረ  መሆኑ ተገልጿል። የጆ ባይደን አስተዳደርም ሆነ የህግ አውጪ አካላት ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችል የጋራ መግባባት ላይ እስካሁን አልደረሱም።በሜክሲኮን አቋርጠዉ ወደ አሜሪካ ከሚገቡት ፍልሰተኞች መካከል ከኮሎምቢያ፤ ከኪዮባ፤ ከቪንዝዌላ እንዲሁም ከኒካራግዋ የሚመጡት ፍልሰተኞች በቁጥር ቀዳሚዉን ሥፍራ የያዙ መሆናቸዉም ታዉቋል። 

USA Mexiko Migration Grenze Title 42
የፍልሰተኞች ቀዉስ በአሜሪካምስል PATRICK T. FALLON/AFP

ከኮቪድ 19 ጋር ተያይዞ የወጣው  የስደተኞች እገዳ መነሳቱን ተከትሎ አሜሪካ በስተኞደተኞች ማዕበል ቀውስ ውስጥ ገብታለች ። ችግሩ ከድንበር ከተሞች አልፎ ሌሎች ግዛቶችንም ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ውስጥ እየጨመረ መሆኑ ተገልጿል። የጆ ባይደን አስተዳደርም ሆነ የህግ አውጪ አካላት ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችል የጋራ መግባባት ላይ አልደረሱም። 
አንቀጽ 42 የኮቪድ 19 ወረርችኝን ለመግታት የሚደረገው ጥረት አንድ አካል ሆኖ የወጣ ህግ ነው። ህጉ ለወትሮው በአሜሪካ ድንበርሮች በኩል የመጡ ስደተኞችን የጥገኝነት ጥያቄ መቀበልን አስቁሞ ወደ ሚክሲኮ እንዲመለሱ ያደርግ ነበር። ባለፈው ሳምንት ይሄው ህግ ማብቃቱን ተከትሎ በርካታ ስደተኞች ወደ አሜሪካ መጉረፍ ጀምረዋል። ከነዚሁ ስደተኞች ውስጥ አንዱ ሳቭየር ካስትሮ የድንበር መሻገሩ ሂደት ከባድ ፈተናን ያካተተ መሆኑን ተናግሯል። 
ይሄ የስደተኞች ማዕበል አሜሪካውያንን፣ የጆ ጋይደን አስተዳደርን እና የህግ አውጪውን አካላት አስጨንቋል። በካሊፎርኒያ ግዛት ነዋሪ የሆኑት የህግ ባለሞያው አቶ ሙሉቃል ታደሰ ጠና ይሄንን ችግር ለመፍታት ሁለቱም ፓርቲወች በባይደን አስተዳደር ላይ የሚያደርጉት ጫና እና የመፍትሄ ሃሳብ ፖለቲካዊ እይታቸውን ያንጸባረቀ እንደሆነ ገልጸዋል። ሪፐብሊካኑ ይሄው የእገዳ ህግ እንደጸና እንዲቀጥል የሚፈልጉ ሲሆን፣ ዲሞክራቶቹ በበኩላቸው አስተዳደሩ አሁን የተከሰተውን ችግር ለመፍታት እየወሰደ ያለው እርምጃ እና ለመተግበር ያሰባቸው አዳዲስ ደንቦች በጣም ጥብቅ ሆነዋል ሲሉ ይሟገታሉ። በዚህም መሰረት በዲሞክራቶች በኩል ካሊፎርኒያ ውስጥ በአስተዳደሩ ላይ ክስ ተመስርቶ በመታየት ላይ መሆኑን አቶ ሙሉቃል ጠቁመዋል።

የጆ ባይደን አስተዳደር ችግሩን ለመፍታት በቂ ዝግጅት አላረገም የሚል ክስ ከሁሉም አቅጣጫ እየቀረበበት ይገኛል። የሃገር ደህንነት ሚኒስትሩ አሌሃንድሮ ማዮርካ ስር በሰደደና ዘመናትን በተሻገረ ችግር ውስጥ ባለ የስደተኞች ህግ ማእቀፍ ውስጥ የምንችለወን እየሰራን ነው ሲሉ ተናግረው የተወካዮች ምክር ቤት አስተዳደሩ የሚያስፈልጉተን እና የጠየቃቸውን ድጋፎች አለመስጠቱ ችግሩን እንዳባባሰው ጠቁመዋል። 
የስደተኛ አስተዳደር ጉዳይ ለረጅም ጊዜያት ከዘለቁ የሁለቱ ፓርቲወች የፖለቲካ ፍጥጫና ልዩነት መገለጫወች ውስጥ አንዱ ነው። የዚህ የስደተኞች ቀውስ ገፈት ቀማሽ ከሆኑት የአሚሪካ ግዛቶች አንዷ በሆነችው ቴክሳስ ውስጥ የምትኖረው ቅድስት ሰማቸው የስደተኞቹ ቁጥር በማቆያ ቦታወች እየጨመረ መምጣቱን እና በድንበር አካባቢ ባሉ ከተሞች ውስጥ የተለያዩ የኢኮኖሚ ተጽኖወች እንዳመጣ ገልጻለች። 
የስደተኞቹ መበርከት ከወሰን ግዛቶች አልፎ በተለያዩ የአሜሪካ ከተሞች ላይ ጫና መፍጠሩ አልቀረም። በተለይ ለስደተኞች መልካም አቀባበል በማድረግ የሚታወቁ እንደ ኒውዮርክ፣ ሎሳንጀለስ፣ ቺካጎ፣ ዴንቨርና ዋሽንግተን ዲሲን የመሳሰሉ ከተሞችም ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጫና እያጋጠማቸው መሆኑን የህግ ባለሞያው አቶ ሙሉቃል ገልጸዋል። 
ከደቡብ የአሜሪካ ወሰን የሚደረገው የስደተኞች ፍልሰት የአሜሪካ ቋሚ ራስ ምታት ሆኖ ዘመናትን ተሻግሯል። 63 በመቶ የሚሆኑት ስደተኞች ሜክሲኮን አቋርጠው ወደ አሜሪካ የሚያቀኑ፣ የሶስተኛ ሃገራት ዜጎች ናቸው። ኮሎምቢያ፣ ኩባ፣ ኒካራጓና ቬንዝዌላ በቁጥር ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛሉ። 

USA Mexiko Grenze/Migranten nutzen Züge um in die USA illegal einzuwandern
የስደተኞች ጎርፍ በአሜሪካምስል Jose Luis Gonzalez /REUTERS

አበበ ፈለቀ
አዜብ ታደሰ 
ኂሩት መለሰ