Eshete Bekeleቅዳሜ፣ ጥቅምት 23 2017የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት በኦሮሚያ ክልል በተፈጸሙ ጥቃቶች 120 የመንግሥት ወታደሮች ገድያለሁ አለ። ህወሓት በፕሪቶሪያ ግጭት የማቆም ሥምምነት የገባቸውን ግዴታዎች እየፈጸመ አይደለም ሲል የኢትዮጵያ መንግሥትን ከሰሰ። አሜሪካ “ታሪካዊ“ ያለችው “የርስ በርስ ጦርነት ያቆመ ሥምምነት“ የተፈረመበትን ሁለተኛ ዓመት በማስመልከት በኢትዮጵያ ግጭት እንዲቆም ጥሪ አቅርባለች። የወባ ወረርሽኝ በኢትዮጵያ ዋንኛ የሕብረተሰብ ጤና ተግዳሮት እንደሆነ የዓለም ጤና ድርጅት አስጠነቀቀ። ከታኅሳስ 22 ቀን 2016 እስከ ጥቅምት 10 ቀን 2017 ብቻ 7.3 ሚሊዮን የወባ ሕሙማን መመዝገባቸውን፤ 1157 ሰዎች መሞታቸውን አስታውቋል።