1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የፖለቲካ አለመረጋጋት እና ትምህርት

እሑድ፣ ኅዳር 17 2010

በኦሮሚያ እና በሶማሌ ክልሎች የተፈጠረው የፖለቲካ አለመረጋጋት መዘዝ በተለያዩ ሁኔታዎች ታይቷል። ከነዚህም አንዱ አንዱ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እና የትምህርት አሰጣጡን ሂደት ይነካል። የፖለቲካ አለመረጋጋቱ ተፅዕኖ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እና በትምህርት አሰጣጡ ሂደት ላይ በሚል ውይይት አካሂደናል።

https://p.dw.com/p/2oDtC
12.06.2013 DW Online Karten Basis Äthiopien Englisch

የመማር ማስተማሩ ሂደት እክል ገጥሞታል

በኦሮሚያ እና ሶማሌ አጎራባች ክልሎች  የተፈጠረው  ለበርካቶች ሞትና በአስር ሺዎች መፈናቀል ምክንያት በሆነው ግጭት  እና  በሰበቡ  እና ካለፉት በተካሄዱተቃውሞ ሰበብ  በሁለቱም ክልሎች  የሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ላይ ጉዳት ደርሷል፣ በክልሎቹ በተፈጠረው አለመረጋጋትም ትምህርት በአግባቡ የሚሰጥበት ሂደት እክል እንደገጠመው እና አሁንም ቢሆን ተማሪዎች እንደሚፈለገው ትምህርታቸውን መከታተል እንዳልቻሉ ጉዳዩ ያሳሰባቸው ተማሪዎች ይናገራሉ። የኦሮሚያ ክልል ተማሪዎች ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች ለደህንነታቸው አስጊ ነው በሚል ወደ ዩኒቨርሲቲው መሄድ የለባቸውም በማለት በተለያዩ የኦሮሚያ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች ተቃውሞ ማድረጋቸው ይታወሳል።

 

አርያም ተክሌ

ማንተጋፍቶት ስለሺ