61 ኛዉ አለም አቀፍ የሲኒማ መድረክ- በርሊናለ
ሐሙስ፣ የካቲት 3 2003ማስታወቂያ
በርሊናለ የፊልም ማዕከል በአሜሪካዊዉ የጦር መኮንን ከተቋቋመ ከአንድ አመት በኳላ ከ 1951 እስከ 1966 አ.ም ድረስ የበርሊን ከንቲባ የነበሩት ከዝያም የምዕራብ ጀርመን ርእሰ ብሄር የነበሩት ቪሊ ብራንት ዛሪ በበርሊን የአለም አገራት የተለየ ባህልን፣ ፖለቲካን፣ ነቀፊታን አልያም ተጽኖን የሚያንጸባርቁ የተለያዩ እዉቀቶችን ያዘሉ ፊልሞች ለህዝብ ለእይታ እንዲበቁ መሰረቱ ጥለዉ ዛሪ በርሊናለ የሲኒማ መድረክ በአለም አሉ ከሚባሉት አንዱ የፊልም ማዕከል ሆንዋል።
ከዛሪ የካቲት ሶስት እስከ የካቲት አስራ ሶስት ድረስ የሚዘልቀዉ በርሊናለ የፊልም ትዕይንት ከአለም አገራት የተሰባሰቡ 385 ያህል ፊልሞችን ለህዝብ ለማሳየት እና ለመገምገም ብሎም አሸናፊ ለሆነዉ ፊልም እና የፊልም ተዋናይ ሽልማትን ለመስጠት የሲኒማ መድረኩን ለስድሳ አንደኛ ግዜ ለመክፈት ዝግጅቱን አጠናቆአል። በለቱ ዝግጅታችን ዛሪ ምሽት ላይ በደማቅ የሚከፈተዉን የበርሊንኑን የፊልም ትዕይንት በርዕስነት ይዞአል። በቅድምያ ግን ሰሞኑን በጀርመን የነበሩ አበይት ባህል ነክ ዜናዎችን በማስቀደም መሰናዶዉን ይጀምራል መሰናዶዉን ያድምጡ!
አዜብ ታደሰ
አርያም ተክሌ