Eshete Bekeleዓርብ፣ ግንቦት 2 2016እናት ፓርቲ እና መኢአድ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ አፋር፣ ሶማሌ እና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች በሚቀጥለው ወር ከሚካሔደው ምርጫ ራሳቸውን አገለሉ። የፍልስጤምን የተባበሩት መንግሥታት አባልነት የጸጥታ ጥበቃው ምክር ቤት እንዲቀበል የድርጅቱ ጠቅላላ ጉባኤ ጠየቀ። በደቡብ አፍሪካ በግንባታ ላይ የነበረ ሕንጻ ሲደረመስ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 12 ደረሰ። በቻድ ምርጫ ጄኔራል ማሕማት ኢድሪስ ዴቢ ማሸነፋቸው ሲሰማ ደስታቸውን ለመግለጽ አደባባይ ከወጡ ሰዎች መካከል የተወሰኑት ለፌሽታ በተተኮሰ ጥይት ሲገገደሉ በርካቶች ቆሰሉ። እስራኤል በራፋሕ የምታደርገው ዘመቻ ከፍተኛ ሰብአዊ አደጋ እንደሚያስከትል አንቶኒዮ ጉቴሬዝ አስጠነቀቁ።