1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ለሰላም የውይይት እና የመነጋገር ጥሪ

ሰኞ፣ መስከረም 7 2016

በሌላ በኩል ትጥቅ አንስተው ከመንግሥት ጋር ውጊያ ውስጥ የገቡ ኃይላትን ለማነጋገር እየትንቀሳቀሰ መሆኑን ደጋግሞ እየገለፀ ያለውና በብዙዎች ዘንድ እየተጠበቀ ያለው ብሔራዊ የምክክር ኮሚሽን አቅርቦት የነበረው "አስቸኳይ ሀገራዊ ጥሪ" በጎ ምላሽ እያገኘበት መሆኑን አስታውቋል።

https://p.dw.com/p/4WULb
Äthiopien   Ethiopian political parties joint council
ምስል Solomon Muchie/DW

ለሰላም የውይይት እና የመነጋገር ጥሪ

ኢትዮጵያ ከተጋረጠባት ውስብስብ የፀጥታ እና የደህንነት መናጋት እንዲሁም የሰላም ማጣት ችግር እንድትወጣ መንግሥት እና ገዢው ፓርቲ ለድርድር እና ለውይይት አማራጮች ቅድሚያ እንዲሰጡ ዶቼ ቬለ ያነጋገራቸው የፖለቲካ ድርጅቶች ጠየቁ። 

የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤትን ጨምሮ ሀሳብ እንዲሰጡ ተጠይቀው ምላሽ ከሰጡት የፖለቲካ ድርጅቶች ውስጥ ሁለቱ ፓርቲዎች የሰላም ጥሪ ሳያደርጉ የቀሩበት ጊዜ እንደሌለ በመግለጽ በተለይ በትጥቅ ውጊያ ችግሮች ይፈታሉ ብሎ መንቀሳቀስ የዜጎችን ሕይወት ከማወኩ በላይ ሀገርን ልከፋ አደጋ የሚያጋልጥ በመሆኑ እውነተኛ ንግግር እንዲጀመር ጠይቀዋል። 

በሌላ በኩል ትጥቅ አንስተው ከመንግሥት ጋር ውጊያ ውስጥ የገቡ ኃይላትን ለማነጋገር እየትንቀሳቀሰ መሆኑን ደጋግሞ እየገለፀ ያለውና በብዙዎች ዘንድ እየተጠበቀ ያለው ብሔራዊ የምክክር ኮሚሽን አቅርቦት የነበረው "አስቸኳይ ሀገራዊ ጥሪ" በጎ ምላሽ እያገኘበት መሆኑን አስታውቋል።

 በተለይ በትጥቅ ውጊያ ችግሮች ይፈታሉ ብሎ መንቀሳቀስ የዜጎችን ሕይወት ከማወኩ በላይ ሀገርን ልከፋ አደጋ የሚያጋልጥ በመሆኑ እውነተኛ ንግግር እንዲጀመር ጠይቀዋል። 
የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤትን ጨምሮ ሀሳብ እንዲሰጡ ተጠይቀው ምላሽ ከሰጡት የፖለቲካ ድርጅቶች ውስጥ ሁለቱ ፓርቲዎች የሰላም ጥሪ ሳያደርጉ የቀሩበት ጊዜ እንደሌለ ተናግረዋል። በተለይ በትጥቅ ውጊያ ችግሮች ይፈታሉ ብሎ መንቀሳቀስ የዜጎችን ሕይወት ከማወኩ በላይ ሀገርን ልከፋ አደጋ የሚያጋልጥ በመሆኑ እውነተኛ ንግግር እንዲጀመር ጠይቀዋል። ምስል Solomon Muchie/DW

አዲሱ ዐመት ከጅምሩ ምን እየተስተዋለበት ነው ? 

በኢትዮጵያ በአዲሱ ዐመት ሰላም እንዲሰፍን በተለያየ የሥራ ዘርፍ የተሰማሩ ግለሰቦችና ተቋማት ሁሉም ለዚህ ስኬት እንዲጥር ያልተቋረጠ ጥሪ አድርገዋል። ዐመቱ ግን እንዳለፈው ሁሉ ገና ከጅምሩ የትጥቅ ግጭት ዜናዎች ያልከሰሙበት ፣ የንፁሃን ዜጎች ሞት የተሰማበት፣ ሃይማኖትን መነሻ ያደረጉ ግጭቶች የተደመጡበት ነው። "በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች እየታዩ ያሉ ደም አፋሳሽ ግጭቶች የኮሚሽኑን ሥራ አዳጋች እያደረጉት ይገኛሉ" በማለት አስቸኳይ ያለውን ሀገራዊ ጥሪ አቅርቦ የንበረው ብሔራዊ የምክክር ኮሚሽን ጥሪው ግቡን መትቶ እንደሆን ተጠይቆ ከተቋሙ የሥራ ኃላፊዎች አንዱ ዶክተር ዮናስ አዳዬ ተስፋ ያለው በጎ ምላሽ መኖሩን ገልፀዋል። 

"የሰላም ጥሪ አቅርባችኋል። ምላሽስ ምንድን ነው ? እኛ እንግዲህ ምላሹን መለኪያውን እስካሁን ድረስ በተለይ አዘግልጅተን እየተከታተልን ባይሆንም፣ በጎ ነው ብለን ነው እያየን ያለነው" የተቃዋሚ ፓርቲዎች ማሳሰቢያ እና የብሔራዊ ምክክር ኮሚሽን ምላሽ

ለአዲስ ዐመት የቀረቡ የሰላም ጥሪዎች ተጨባጩ  እውነታ 

የ ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ ሊቀመንበር ሰሞኑን ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በፃፉት ግልጽ ደብዳቤ "የሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ፓርቲዎ እና መንግስትዎ እናሳካለን ብለው ለሕዝብ ከሚነግሩት እውነተኛ የብልጽግና ጉዞ እየተለየ መጥቷል" በማለት እርምት እንዲደረግ ይብጃል ያሉትን ጠይቀዋል።
መሠረታዊ የሀገር ችግሮች በንግግር እንዲፈቱ ጥረት ያላደረግንበት ጊዜ የለም የሚሉት ካነጋገርናቸው ፓርቲዎች መካከል የኦፌኮ ምክትል ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ሙላቱ ገመቹ ኃይልን የችግር መፍቻ አማራጭ ከማድረግ ልማድ እንዲወጣ ጠይቀዋል። 

"ልዩነቶች አሁን በ 21 ኛው መቶ ክፍላ ዘመን ላይ በጉልበት ፣ በጠብመንጃ ኃይል ፣ በውጊያ የምናመጣው ነገር የለም። እርስ በርስ በተፈጠረው ግጭት እልቂት እየተፈጠረ ነው። ከዚህ በፊት ያለማነውን ልማት በሙሉ እያወደምን ነው። ሁሉም ለሰላም ታጥቆ መነሳት አለበት"በኢትዮጵያ የታሪክ ትርክት ላይ ያተኮረው የውይይት መድረክ


አዲስ ዐመትን አስታከው የሃይማኖት ተቋማት፣ ግለሰቦች እና ድርጅቶች ያደረጓቸው ጥሪዎች ፍሬ ያመጡ ስለመሆን አለመሆናቸው በግልጽ ለመናገር የሚቸግር ይመስላል።
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በተለይ በአማራ ክልል ከሕግ ወይም ከፍርድ ውጪ የሚፈፀሙ ግድያዎች፣ የንፁሃን ዜጎች መጎዳትና የንብረት ውድመት አሳሳቢ ስለመሆኑ ከሰሞኑ ገልጿል። የእናት ፓርቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሰይገሥላሴ አያሌው ለቀረብላቸው ጥያቄ ምላሽ ከሰጡት ውስጥ አንዱ ናቸው። 

"ሁሉን አቀፍ የሚመስል የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ እየገባን ነው ያለነው። ስለዚህ ከዚህ ውስጥ መውጫውን መንገድ መፈለግ ምቻል አለብን። የመፍትሔው አካል መሆን አለብን የሚለውን ከመንግሥት የሰማነው ነገር የለም። ያ ባልሆነበት ለውጥ አንጠብቅም" 

በብዙዎች ዘንድ እየተጠበቀ ያለው ብሔራዊ የምክክር ኮሚሽን አቅርቦት የነበረው "አስቸኳይ ሀገራዊ ጥሪ" በጎ ምላሽ እያገኘበት መሆኑን አስታውቋል።
ብሔራዊ የምክክር ኮሚሽን በሌላ በኩል ትጥቅ አንስተው ከመንግሥት ጋር ውጊያ ውስጥ የገቡ ኃይላትን ለማነጋገር እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ደጋግሞ እየገለፀ ነው። ምስል Solomon Muchie/DW

ብልጽግና እና ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምን አሉ 


የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች አዳማ ለስብሰባ የተቀመጡት ገዢው ብልፅግና ፓርቲ  "በሁሉም የሀገራችን ክፍሎች በዘላቂነት ሰላምን ለማረጋገጥ እንዲቻል ውጤታማ የሆኑ ስትራቴጂዎችን በመንደፍ ግጭቶችን ማምከን፣ ሊፈጠሩ የሚችሉ ማህበራዊ ቀውሶችን ማምከን ችለናል"። ሲል ዛሬ ገልጿል።
የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሥራ አስፈፃሚ አባል ዶክተር መብራቱ አለሙ እንደሚሉት ግን በመንግሥትም ሆነ በገዢው ፓርቲ በኩል ውጥረቶችን በሰላም ለመፍታት ቁርጠኝነት ያሻል። ተቃውሞ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት መግለጫ ላይ

" ቁርጠኝነት ያስፈልጋል። መንግሥት በጣም ቁርጠኛ መሆን አለበት። ገዢው ፓርቲ በጣም ቁርጠኛ መሆን አለበት። ለለውጥ መዘጋጀት አለበት። ለድርድር ራሱን ክፍት ማድረግ አለበት" 
የምኁራን እና ተንታኞች ከመናገር መቆጠብ 

ኢትዮጵያ ውስጥ በሚስተዋሉ ወቅታዊ የፖለቲካ ሁነቶች፣ ችግሮች እና መፍትሔዎቻቸው ላይ የበሰለ ሀሳባቸውን በገለልተኝነት ያጋሩ የነበሩ የፖለቲካ ባለሙያዎች አሁን አሁን ድምፃቸው አይሰማም። እኛም በዚህ ዘገባ ላይ የመፍትሔ ሀሳቦችን እንዲያካፍሉ ከጋበዝናቸው ሰዎች አብዛኞቹ ፈቃደኛ ሊሆኑ አልቻሉም።

ሰሎሞን ሙጬ 

ኂሩት መለሰ

ማንተጋፍቶት ስለሺ