1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ልማትና የቤቶች መፍረስ

ሐሙስ፣ ግንቦት 16 2004

ከተማን ለማልማትና ለመገንባት በሚል መርህ በአዲስ አበባም ሆነ በክፍለ ሐገር የሚገኙ ቤቶች እየፈረሱ እንደሆነ፤ በመፍረስ ላይ ያሉትም ጥቂት እንዳልሆኑ የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ጌታቸዉ ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ የላከዉ ዘገባ ያስረዳል። እንደዘገባዉም

https://p.dw.com/p/1524p

ሂደቱ ፈጣን በመሆኑ ባስቸኳይ በሚወሰዱ ርምጃዎች ቤት የፈረሰባቸዉ በርካታ ኗሪዎች መጠለያ ፍለጋ በመንከራተት ላይ ይገኛሉ። ከፈረሱና እንዲፈርሱ ከተወሰነባቸዉ በጥንታዊነታቸዉ የታወቁና በቅርስነት ሊመዘገቡ የሚገባቸዉ ቤቶች ይገኛሉ። ከእነዚህ መካከልም በአራት ኪሎ ባሻ ወልዴ ችሎት ተብሎ በሚጠራዉ አካባቢ የሚገኘዉ ተስፋ ገብረስላሴ ዘብሄረ ቡልጋ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ወደአንድ መቶ ዓመታት ገደማ ያስቆጠረዉ ማተሚያ ቤት እና በሸራተን አዲስ ሆቴል ጀርባ የፈረሰ የጥንት ቤት ይጠቀሳሉ።

ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ

ሸዋዬ ለገሠ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ