"መለያየት እና መገፋፋት" ለኢትዮጵያውያን አያዋጣም አቶ ሽመልስ አብዲሳ
ቅዳሜ፣ ሚያዝያ 26 2011በሀገሪቱ የተካሄደውን ለውጥ ተከትሎ በተለያዩ ክልሎችና ክልሎቹ በሚዋሰኑባቸው አካባቢዎች የተፈጠሩ ችግሮችን ማረጋጋትና ወደ ነበረበት መመለስ ዛሬም የቤት ስራ እንደ ሆነ ቀጥሏል። ከለውጡ ጋር ወደ ስልጣን የሚመጡ ሹማምንት የተፈናቀሉ ዜጎችን ማደራጀት፣ የተቋረጡ የህዝቦች የእርስ በእርስ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነቶችን ወደ ቀድሞ ማስመለስ በሚል አጀንዳ የሚከውኑት ተግባር ለዚህ አንዱ ማሳያ ነው፡፡ ሰሞኑን የኦሮሚያ ፣ ሶማሌ እና ሀረሪ ክልላዊ መስተዳድሮች እና የህብረተሰቡ ተወካዮች የተገኙበት መድረክ ተካሂዷል፡፡
በዚህ መድረክ በተለይ የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፋ መሀመድ ከህዝብ ለህዝብ ትስስሩ በተጨማሪ ተቋርጠው የነበሩ የንግድ እንቅስቃሴዎች በአፋጣኝ መጀመር እንዳለባቸው በአፅንኦት ገልፀዋል፡፡
አቶ ሙስጠፋ በንግድ እንቅስቃሴ ተጠቃሚ የሚሆነው አንድ ወገን ብቸ አለመሆኑን ጠቁመው በክልሉ በኩል ለንግድ እንቅስቃሴ መጀመር ዝግጁ መሆናቸውና በእንቅስቃሴውም ምንም ዓይነት ገደብ ሊኖር እንደማይገባ አስታውቀዋል፡፡ በሀገሪቱ በተካሄደው ለውጥ ዋነኛ መሪ እንደሆኑ የሚነገርላቸው አቶ ለማ መገርሳ በመከላከያ ሚንስትርነት መሾምን ተከትሎ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መሰረተዳድር ሆነው በመሾም ሀላፊነት የተረከቡት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ከበዓለ ሲመታቸው ማግስት ጀምሮ ማካሄድ የጀመሩት የህዝብ ልህዝብ አንድነትን የማጠናከር ጥረት በክልሉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል በዚሁ መድረክ ጠቁመዋል።
በሀረር በተካሄደው በዚሁ መድረክ ተጎራባች በሆኑት አካባቢዎች መካከል ያለውን የቆየ አንድነትና ትስስር በማጞልበት በኩል የሀረሪ ክልል የበኩሉን ኃላፊነት እንደሚወጣ የክልሉ ርእሰ መስደዳድር አቶ ኡርዲን በድሪ ተናግረዋል።
መሳይ ተክሉ
እሸቴ በቀለ