ለሻምፒዮንስ ሊግ ግማሽ ፍጻሜ ሪያል ማድሪድ ከባዬርን ሙይንሽን
ረቡዕ፣ ሚያዝያ 30 2016ማስታወቂያ
በሻምፒዮንስ ሊግ የደርሶ መልስ የግማሽ ፍጻሜ ግጥሚያ ዛሬ ማታ የጀርመኑ ባዬርን ሙይንሽን ከስፔኑ ሪያል ማድሪድ ጋ ይጋጠማል ። ትናንት በነበረው ጨዋታ ሌላኛው የጀርመን ቡድን ቦሩስያ ዶርትሙንድ የፈረንሣዩ ፓሪ ሳን ጃርሞን 1 ለ0 አሸንፏል ። በደርሶ መልስ የ2 ለ0 ውጤትቱም ቦሩስያ ዶርትሙንድ እንግሊዝ ዌብሌይ ስታዲየም ውስጥ ግንቦት 24 ለሚካሄደው የፍጻሜ ውድድር ማለፉን አረጋግጧል ። ባዬርን ሙይንሽን በሜዳው አሊያንትስ አሬና ስታዲየም ባደረገው ግጥሚያ የተለያየው በሁለት እኩል ውጤት ነበር ።
ዛሬ ማታ ሪያል ማድሪድን በሜዳው ሳንቲያጎ ቤርናቤዉ ይገጥማል ። ባዬርን ሙይንሽን ዛሬ ማታ ማሸነፍ ከቻለ፦ ሁለቱ የጀርመንቡድኖች ለፍጻሜ በመድረስ እንደ ጎርጎሪዮስ አቆጣጠር በ2013 የነበራቸው ታሪክ ይደገማል ማለት ነው ። በወቅቱ በፍጻሜው ባዬርን ሙይንሽን ቦሩስያ ዶርትሙንድን በአሪዬን ሮበን የመጨረሻ ደቂቃ ግብ 2 ለ1 አሸንፎ ዋንጫ ወስዶ ነበር ።
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ዮሐንስ ገብረ-እግዚአብሔር