ከሞቱት 3ቱ ጋዜጠኞች ነበሩ
ቅዳሜ፣ ታኅሣሥ 13 2011ማስታወቂያ
በሶማሊያ መዲና ሞቃዲሾ ሁለት በተሽከርካሪ ላይ የተጠመዱ ቦምቦች ፈንድተው ከአስር በላይ ሰዉ ገደሉ። እንደ ፖሊስ ገለፃ በጥቃቱ ቢያንስ 16 ሰዎች ሲገደሉ በርካቶች ቆስለዋል። ፍንዳታው የደረሰው በቤተ መንግስት አቅራቢያ ሲሆን ጥቃት ሰንዛሪዎቹም ሁለት አጥፍቶ ጠፊዎች ናቸው ተብሏል። ለዚህም ጥቃት ራሱን እስላማዊ መንግስት ሲል የሚጠራው ቡድን ኃላፊነት ወስዷል። ከሟቾቹ መካከል ታዋቂ ጋዜጠኛ አዊል ዳሂር ሳላድን ጨምሮ መቀመጫውን ለንደን ያደረገው የዮንቨርሳል ቲ ቪ ሶስት ባልደረቦች እንደሚገኝበት ፖሊስ ገልጿል። ከቆሰሉት ሰዎች መካከል ደግሞ የሞቃዲሾ ምክትል ከንቲካ ይገኙበታል። እነዚህ ሁለት ጥቃቶች የደረሱት በሶማሊያ የሚንቀሳቀሰው የአል-ሸባብ ቡድን ራሱን እስላማዊ መንግሥት ብሎ የሚጠራውን ታጣቂ ቡድን ከሶማሊያ ምድር ጠራርጎ ለማጥፋት ከዛተ ከአንድ ቀን በኋላ ነው።
ልደት አበበ
ነጋሽ መሐመድ