1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በመንግስት የጸጥታ ሐይሎች የሚካሄድ እገታ ማቆሚያው የት ነው?

እሑድ፣ ጥቅምት 24 2017

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ያሉበት ሁኔታ ሳይገለጽ በተራዘመ እስር ውስጥ የሚገኙ በአስገድዶ መሰወር ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ከ52 በላይ ሰዎች አቤቱታ መመርመሩን፤ የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች በተራዘመ እስርና አስገድዶ በመሰወር ከ1 እስከ 9 ወራት አስረው ያቆዩዋቸው ሰዎች መለቀቃቸውን በመግለጫው አትቷል።

https://p.dw.com/p/4mU1Z
"የጸጥታ ሃይሎች አስገድደው ይሰውራሉ፤ያስራሉ የሰብአዊ መብት ጥሰት ይፈጽማሉ" ኢሰመኮ
"የጸጥታ ሃይሎች አስገድደው ይሰውራሉ፤ያስራሉ የሰብአዊ መብት ጥሰት ይፈጽማሉ" ኢሰመኮምስል Fotolia/axentevlad

እንወያይ፤ በመንግስት የጸጥታ ሐይሎች የሚካሄድ እገታ ማቆሚያው የት ነው?

ጥቅምት 13 ቀን 2017 ዓም የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ”መደበኛ ባልሆነ ማቆያ ቦታ ያሉበት ሳይገለጽ እንዲቆዩ የተደረጉና አስገድዶ መሰወር ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ተጎጂዎችና ቤተሰቦቻቸው በተመለከተ ተጠያቂነት ሊረጋገጥና ፍትህ ሊሰጣቸው ይገባል”  በሚል ርእስ መግለጫ አውጥቷል።

ኮሞሚሽኑ በመግለጫው

ያሉበት ሁኔታ ሳይገለጽ በተራዘመ እስርውስጥ የሚገኙ በአስገድዶ መሰወር ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ከ52 በላይ ሰዎች አቤቱታ መመርመሩን፤

 የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች በተራዘመ እስርና አስገድዶ በመሰወር ከ1 እስከ 9 ወራት አስረው ያቆዩዋቸው ሰዎች መለቀቃቸውን፤

በታሰሩበት ጊዚያዊ የማቆያ ሥፍራም በቂ ምግብ፣ ውሃና የንጽህን መጠበቂያ እንደማይቀርብላቸው፤

በአንዳንዶቹ ላይ ድብደባ እንደተፈጸመባቸው፤

ይባስ ብሎም በመካከለኛና በከፍተኛ የመአርግ ደረጃ የሚገኙ የጸጥታ ሐይሉ አባላት የታሰሩትን ለማስለቀቅ ቤዛ መጠየቃቸውን እና የተለያዩ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እንደተፈጸሙባቸው በዝርዝር አቅርቧል። ከዚህ ቀደምም ተመሳሳይ ድርጊቶች በመንግስትየጸጥታ ሐይሎችእንደሚወሰዱና ተጠያቂነት ሊሰፍን እንደሚገባ አስታውሶ እንደነበርም መግለጫው አስታውሷል። በመንግስት የጸጥታ ሐይሎች የሚካሄድ እገታ ማቆሚያው የት ነው? የዛሬ የውይይታችን ርእስ ነው።

በውይይቱ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን፣ በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች እገታ የተፈጸመባት ጋዜጠኛና በፖለቲካ ምክንያት ደረሰብኝ ባሉት ተጽዕኖ ለስደት የተዳረጉ የሕግ ባለሙያ ተሳትፈዋል። የድምጽ ማዕቀፉን በመጫን ሙሉ ዝግጅቱን ያዳምጡ።

ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር