1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ፖለቲካሰሜን አሜሪካ

ስለ ካማላ ሐሪስ የምርጫ ቅስቀሳ መዝጊያ ጎናጭ ንግግር ቃለ-መጠይቅ

ረቡዕ፣ ጥቅምት 20 2017

የዩናይትድ ስቴትስ ቀጣዩ ፕሬዚደንትን ማንነት የሚለይበት አጠቃላይ ምርጫ አንድ ሳምንት ብቻ ቀርቶታል ። የዴሞክራት ፓርቲ እጩ ፕሬዚደንት ተፎካካሪዋ ካማላ ሐሪስ የመዝጊያ ንግግራቸውን ዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ውስጥ ከኤሊፕስ አሰምተዋል ። ካማላ ሐሪስ ዶናልድ ትራምፕ ቢመረጡ አደጋ እንዳለ ጠቁመዋል ። ምን ይሆን? ከቃለ መጠይቁ ያገኙታል ።

https://p.dw.com/p/4mP9a
ዶናልድ ትራም እና ካማላ ሐሪስ
የዩናይትድ ስቴትስ ቀጣዩ ፕሬዚደንትን ማንነት የሚለይበት አጠቃላይ ምርጫ አንድ ሳምንት ብቻ ቀርቶታል ። በዶናልድ ትራም እና ካማላ ሐሪስ መካከል የመራጮች ፍላጎት ድምፅ ልዩነት ካማላ ከአራት መምራታቸው ወደ አንድ በመቶ ወርዷል ። ምስል Susan Walsh/AP/Alex Brandon/dpa/picture alliance

የዩናይትድ ስቴትስ ምርጫ ቅስቀሳ ከወዲሁ ፍጥጫ ተስተውሎበታል

የዩናይትድ ስቴትስ ቀጣዩ ፕሬዚደንትን ማንነት የሚለይበት አጠቃላይ ምርጫ አንድ ሳምንት ብቻ ቀርቶታል ። ከወዲሁ የዴሞክራት ፓርቲ እጩ ፕሬዚደንት ተፎካካሪዋ ካማላ ሐሪስ የመዝጊያ ንግግራቸውን ዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ውስጥ ከኤሊፕስ አሰምተዋል ።

ካማላ የመዝጊያ ንግግራቸውን ማክሰኞ ምሽት ያሰሙበት ኤሊፕስ ስፍራ የቀድሞው ፕሬዚደንት የአሁኑ ተፎካካሪያቸው ሪፐብሊካኑ ዶናልድ ትራምፕ ባለፈው ምርጫ ተጭበርብሯል በሚል ደጋፊዎቻቸው እስከመጨረሻው ድረስ እንዲፋለሙ ያበረታቱበት ነው ።

ካማላ ሐሪስ ለመዝጊያ ንግግራቸው ኤሊፕስ ሥፍራን የመረጡት እንደ ጎርጎሪዮስ አቆጣጠር በ2021 ስፍራ ከዩናይትድ ስቴትስ ምርጫ፤ የዶናልድ ትራምፕ ንግግር እና የአመጽ ድርጊቶች ጋር በመያያዙ መሆኑን የአታላንታው ዘጋቢያችን ታሪኩ ኃይሉ በቃለ መጠይቁ ገልጧል ።  ለኢትዮ አሜሪካውያን መራጮች የቀረበው ጥሪ

«ከ90 ቀናት በኋላ እኔ ወይንም ዶናልድ ትራምፕ ወደ እንቁላሉ ጽ-ቤት እንገባለን » ያሉት ካማላ ሐሪስ ዶናልድ ትራምፕ ቢመረጡ ተራ ዜጎችን ሳይቀር ሊያጠቋቸው የሚፈልጓቸውን ስሞች ዝርዝር ይዘው ነው ወደ ቤተመንግሥቱ የሚገቡት ብለዋል።  ስለራሳቸው ሲናገሩም፦ «እኔ ስመረጥ በመጀመሪያው ቀን ለአሜሪካ ነዋሪዎች የምሠራላቸውን ሙሉ ለሙሉ ቅድሚያ የሚያስፈልጋቸውን ዝርዝሮች ይዤ ነው የምገባው» ሲሉም ተደምጠዋል ።

ካማላ በዚህ ንግግራቸው ከደጋፊዎቻቸውም ሆነ ከነቃፊዎቻቸው የተለያዩ ምላሾችን አግኝተዋል ። በተለይ ግን ፕሬዚደንት ጆ ባይደን የዶናልድ ትራምፕን ደጋፊዎች እጅግ የዘለፉበት ቪዲዮ ከተሰራጨ በኋላ ፍጥጫው አይሏል ። ካማላ ሐሪስ ወደ ምርጫው ሲገቡ ከነበራቸው የመራጮች ድጋፍ የአራት ከመቶ የበላይነት አሁን ልዩነቱ ጠብቦ ወደ አንድ ከመቶ ወርዷል ። 

ዶናልድ ትራምፕ አንድ ቀን ቀደም ብሎ ፍሎሪዳ ከሚገኘው የማር-አ-ላጎ መዝናኛ ስፍራ ካማላ ሐሪስን በፍልሰት እና ኤኮኖሚ ጉዳዮች በብርቱ ተችተዋል ። እሳቸውስ ምን አሉ፤ ከካማላ ሐሪስ የመዝጊያ ንግግር በኋላስ ከእሳቸውም ሆኑ ደጋፊዎቻቸው ምላሹ ምን ይመስል ነበር?

የዩናይትድ ስቴትስ ምርጫስ ወዴት እያመራ ነው ማለት ይቻላል?

ሙሉ ቃለ መጠይቁን ከድምፅ ማእቀፉ ማድመጥ ይቻላል ።

ታሪኩ ኃይሉ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር