ስለ12ኛ ክፍል ፈተና የትምህርት ሚኒስቴር ውሳኔ
ሰኞ፣ ሚያዝያ 10 2014ማስታወቂያ
ባለፈው ዓመት በጦርነት እና ግጭት ቀጣና ውስጥ የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና ወስደው ማለፍ ያልቻሉ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በ2014 ዓ.ም እንደ መደበኛ ተማሪ መፈተን እንዲችሉ ተወሰነ። በጦርነትና በፀጥታ መጓደል ምክንያት በአፋር፣ በአማራ፣ በኦሮሚያ እና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ላጋጠመ የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ውጤት መቀነስ ደግሞ መንግሥት ተጨማሪ የቅበላ አቅም በመፍቀድ ክልሎቹ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆነው ተፈትነዋል ብለው የሚያስቧቸውን ዞኖች አሳውቀው የሚለዩት በ43 ዩኒቨርሲቲዎች እንዲደለደሉ መወሰኑን የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል። ከተማሪዎች ውጤት ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ቅሬታ ከተነሳባቸው ክልሎች ዋነኛው የአማራ ክልል ውሳኔው ስጠብቀው ከነበረው አንፃር በቂ ነው ማለት አንችልም ብሏል። ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በቀጣይ የትምህርት ሥርዓቱ የመንግሥት የፖለቲካ ጥቅም ማሳኪያ እንዳይሆን በማድረግ እና ፈተናን በቴክኖሎጂ አስደግፎ በመስጠት ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠት እንቀሳቀሳለሁ ብሏል።
ሰሎሞን ሙጬ
ሸዋዬ ለገሠ
እሸቴ በቀለ