ስለኮሮና ተሐዋሲ የህክምና ባለሙያዎች ምን ይላሉ?
ማክሰኞ፣ መጋቢት 15 2012ማስታወቂያ
ኮቪድ 19 ማለትም ኮሮና ተሐዋሲ መጀመሪያ በአንድ ሰው ላይ ከታየ በኋላ 100 ሺህ ሰዎችን ለመልከፍ 67 ቀናት እንደወሰደበት፤ ሁለት መቶ ሺህ ለመሙላት ግን ተጨማሪ 11 ቀናት ብቻ እንዳስቆጠረ የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ተናግረዋል። በተሐዋሲው የተያዙ ሰዎች 300 መሙላታቸው በተሰማ ከሁለት ቀናት በኋላ ዛሬ ደግሞ አጠቃላይ ቁጥራቸው 396,236 መድረሱ ይፋ ሆኗል። ኮሮና ተሐዋሲ ባለው የመጋባት ፍጥነት የሚለክፈው ሰው እየጨመረ ስለሚሄድም ምናልባት በቅርቡ በየሃገራቱ የታማሚው ቁጥር 100 ሺህ ሊሞላ እንደሚችል የዓለም የጤና ድርጅት ግምቱን አመላክቷል። ዓለምን አስጨንቆ ያደናገጠው አዲሱ ተሐዋሲ የፍጥነቱን ያህል ተገቢው ጥንቃቄ በተወሰደባቸው እንደቻይና እና ጃፓን ያሉ ሃገራት የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መቀነስ ብቻ ሳይሆን የወትሮው ሕይወት እያንሰራራ መሆኑ ደግሞ በሌላ በኩል እየተሰማ ነው። ፕሮፌሰር ያሬድ ወንድምኩን በዩናይትድ ስቴትሷ ቨርጂኒያ ግዛት የውስጥ ደዌ ህክምና ባለሙያ ናቸው። ሙሉ ቅንብሩን ከድምፅ ማዕቀፉ ያድምጡ።
ሸዋዬ ለገሠ
ኂሩት መለሰ