ስለደቡብ ሱዳን የተመድ እና የአፍሪቃ ህብረት ምክክር
ሐሙስ፣ ጳጉሜን 3 2008ማስታወቂያ
የደቡብ ሱዳናውያን ደህንነት ዋስትናን ለማረጋጋጥ እንዲያስችል ተጨማሪ 4,000 ሰላም አስከባሪዎች በዚያ እንዲሰማሩ የዓለሙ መንግሥታት ድርጅት ከፍተኛ አካል ያስተላለፈውን ውሳኔ የሀገሪቱ መሪዎች መጀመሪያ ላይ ከተቃወሙ በኋላ አሁን መቀበላቸው ተስፋ ሰጪ መሆኑ ተገልጾዋል። ደቡብ ሱዳን ውስጥ እጎአ ከ2011 ዓም ወዲህ 12,000 ሰላም አስከባሪዎች ተሰማርተዋል። የተጨማሪዎቹ ሰላም አስከባሪዎች ስምሪት ዝርዝር ከደቡብ ሱዳን መንግሥት ጋር በጋራ የሚዘጋጅ መሆኑን የተመድ እና አፍሪቃ ህብረት ባለስልጣናት አስታውቀዋል።
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
አርያም ተክሌ
ነጋሽ መሀመድ