1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ቃለ መጠይቅ፣ የሶማሊያና የግብፅ ወታደራዊ ዝግጅት ያስከተለዉ ሥጋት

Negash Mohammedረቡዕ፣ ነሐሴ 29 2016

ግብፅ ከዚሕ በተጨማሪ በመጪዉ ታሕሳስ ባዲስ መልክ ይዋቀራል ለተባለዉ በሶማሊያ የአፍሪቃ ሕብረት ሠራዊት 5000፣ ለሶማሊያ መንግሥት በቀጥታ ድጋፍ የሚሰጥ ሌላ 5000 ጦር ኃይል ሶማሊያ ዉስጥ ለማስፈር ማቀዷም በሰፊዉ እየተነገረ ነዉ።የሶማሊያና የግብፅ ጦር ኃይላት የጋራ ወታደራዊ ልምምድ ለማድረግ እየተዘጋጁ መሆናቸዉም ተነግሯል

https://p.dw.com/p/4kGfa

ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የመንግሥትነት እዉቅና የሌላት የሶማሊላንድ ወደብን ለመኮናተር የመግባቢያ ስምምነት መፈራረሟን ያስከተለዉ መዘዝ አካባቢዉን ከሌላ ፍጥጫ ከትቶታል።ኢትዮጵያ የሶማሊያን ልዑላዊ ግዛት «ደፍራለች» ያሉት የሶማሊያ ፌደራዊ ሪፐብሊክ መንግሥት (ሞቃዲሾ) መሪዎች አጋጣሚዉን አዳዲስ ወዳጅና ድጋፍ ለማግኘት እየተጠቀሙበት ነዉ።የሞቃዲሾ መሪዎች ከቱርክና ከግብፅ ጋር ወታደራዊ ስምምነት ተፈራርመዋል።

ቱርክ ሁለቱን መንግስታት ለማስታረቅ ማደራደር መጀመሯ የሞቃዲሾ መሪዎችን የሚያረካ አይነት አልሆነም።ከዚሕ ቀደም አንካራ ላይ ቢያንስ ሁለቴ የተደረገዉ ድርድር ለሁነኛ ዉጤት ባይበቃም ድርድሩ በያዝነዉ መስከረም ወር እንደሚቀጥል የቱርክ ባለስልጣናት አስታዉቀዋል።

የአንካራዉ ቀጠሮ ሲጠበቅ፣ የድርድሩ ሒደት እንዴትነት ሲያጠያይቅ ባለፈዉ ሳምንት ማክሰኞ ግብፅ ለሶማሊያ የመጀመሪያዉን የጦር መሳሪያ ልካለች።C-130 የተባሉት ሁለት አሜሪካ ሰራሽ ወታደራዊ አዉሮፕላኖች የጫኑት የጦር መሳሪያና ጥይት ዓይነት በዉል አልተነገረም።ይሁና ግብፅ ለሶማሊያ ከምታስታጥቀዉ ጦር መሳሪያ የመጀመሪያዉ እንጂ የመጨረሻዉ እንዳልሆነ በሰፊዉ እየተነገረ ነዉ።

ግብፅ ከዚሕ በተጨማሪ በመጪዉ ታሕሳስ ባዲስ መልክ ይዋቀራል ለተባለዉ በሶማሊያ የአፍሪቃ ሕብረት ሠራዊት 5000፣ ለሶማሊያ መንግሥት በቀጥታ ድጋፍ የሚሰጥ ሌላ 5000 ጦር ኃይል ሶማሊያ ዉስጥ ለማስፈር ማቀዷም በሰፊዉ እየተነገረ ነዉ።የሶማሊያና የግብፅ ጦር ኃይላት የጋራ ወታደራዊ ልምምድ ለማድረግ እየተዘጋጁ መሆናቸዉም ተነግሯል።ኢትዮጵያ የሶማሊያና የግብፅን እርምጃና እቅድ አዉግዛለች።በዚሕ መሐመል ጅቡቲ አስጊዉን ዉዝግብ ለማቃለል ኢትዮጵያ የታጁራ ወደብን እንድትጠቀም ፈቅዳለች።

የዉዝግብ፣ ፍጭጫዉ ንረትና የአካባቢዉ ሐገራትን ፍላጎትና የግብፅን ሚና በተመለከተ የደራሲና የፖለቲካ ተንታኝ ዩሱፍ ያሲንን አነጋግረናል።ሙሉ ቃለ መጠይቁን ያድምጡት።

ነጋሽ መሐመድ

 

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ስለዚሕ ዝግጅት

ስለዚሕ ዝግጅት

DW-Interview mit Frank-Walter Steinmeier
ምስል DW/R. Oberhammerምስል DW/R. Oberhammer

ማሕደረ ዜና

ማሕደረ ዜና፣ ኢትዮጵያን ጨምሮ በመላዉ ዓለም የተደረጉ፣ ሊደረጉ የታቀዱና የተነገሩ ዓበይት ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዘወትር ሰኞ ይቃኙበታል። ዝግጅቱ የሐገራትን፣ የዓለም አቀፍ እና አካባቢያዊ ማሕበራትን፣ድርጅቶችንና የታዋቂ ግለሰቦችን ያለፈ፣ያሁንና የወደፊት ምግባሮችን እያነሳ በባለሙያዎች አስተያየት የተደገፈ ትንታኔ ይቀርብበታል። አዘጋጅ፣ ነጋሽ መሐመድ