ቃለ ምልልስ በጀርመን የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር እስክንድር ይርጋ ጋር፦ክፍል አንድ
ሐሙስ፣ ኅዳር 26 2017በጀርመን አዲሱ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር እስክንድር ይርጋ ፣ሥራቸውን ከጀመሩ አሁን ሁለተኛውን ወር ይዘዋል።በአምባሳደርነት የተሾሙት ባለፈው ዓመት በግንቦት ወር ሲሆን የሹመት ደብዳቤያቸውን ለጀርመን ፕሬዝዳንት ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር ያቀረቡት ደግሞ በዚህ ዓመት በጥቅምት አጋማሽ ላይ ነው።የዳያስፖራ ኢትዮጵያውያንን ተሳትፎ ለማሳደግ ምክክር ተደረገ
አምባሳደር እስክንድር በኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዲፕሎማሲው ዘርፍ ከአታሼነት ተነስተው እስከ መጨረሻው የስራ ሃላፊነት ደርሰዋል። በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከ21 ዓመታት በላይ በተለያዩ የሃላፊነት ዘርፎች ያገለገሉት አምባሳደር እስክንድር ከኢትዮጵያ ውጭ ከጎርጎሮሳዊው 2011 ዓም አንስቶ ለ4 ዓመታት በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በካውንስለርነት፣ ከጎርጎሮሳዊው 2019 ዓ.ም. እስከ 2021 ዓ.ም. በለንደን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከዚያም በበርሊን የኢትዮጵያ ኤምባሲ በኤኮኖሚና በዲፕሎማሲ ዘርፍ በሃላፊነት ሰርተዋል። የጀርመን ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ሆነው እስከተሾሙበት ጊዜ ድረስም በኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአውሮጳና የአሜሪካ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጀነራል በምክትል ዳይሬክተር ጀነራልነት አገልግለዋል።ጠቅላይ ሚንሥትር ዐቢይ በጀርመን ፍራንክፈር ከኢትዮጵያውያን ጋር ሊወያዩ ነው
ዶቼቬለ አምባሳደር እስክንድር ይርጋ በአዲሱ ሃላፊነታቸው ምን ሊያሳኩ እንዳሰቡ፣ጀርመናውያን ኢንቬስተሮችንና ቱሪስቶችን ለመሳብ በሚደረገው ጥረት እንቅፋት ሆኗል ስለሚባለው የሰላም እጦትና ተጨማሪ ተግዳሮች እንዲሁም በሌሎች ጉዳዮች ላይም አነጋግሯቸዋል። ሁለተኛው ክፍል ሳምንት ማክሰኞ ይቀርባል።
የመጀመሪያውን ክፍል ቃለ ምልልስ ለማዳመጥ ከታች የሚገኘውን ማገናኛውን ይጫኑ።
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ