1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በህወሃት መሪዎች መካከል የቀጠለው ውዝግብ

ሐሙስ፣ መስከረም 9 2017

ህወሃት ውስጥ የተፈጠረው ውዝግብ እያደር እየጋለ መሄዱ እየታየ ነው። ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር በተቃራኒ በቅርቡ ስብሰባ ያካሄደው ህወሃት አቶ ጌታቸው ረዳን ጨምሮ የተወሰኑ የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትን ማገዱን ይፋ አድርጓል። አቶ ጌታቸውም ህወሃት የክልሉን ጊዜያዊ አስተዳደር ከሥልጣን ለማውረድ እየሠራ ነው በማለት ከሰዋል።

https://p.dw.com/p/4krPT
በመቀለ የህወሃት ዋና ጽሕፈት ቤት
በመቀለ የህወሃት ዋና ጽሕፈት ቤት ምስል Million Hailesilassie/DW

በህወሃት መሪዎች መካከል የቀጠለው ውዝግብ

 

ሕዝባዊ ወያነ ሀርነት ትግራይ በምህጻሩ ህወሃት ውስጥ የተፈጠረው ውዝግብ እያደር እየጋለ መሄዱ እየታየ ነው። ሰሞኑን ወደ ሽረ ከተማ ተጉዘው ሕዝባዊ ስብሰባ ለማድረግ የሞከሩት የጊዜያዊ መስተዳድሩ ሊቀመንበር ጌታቸው ረዳ ከፍተኛ ተቃውሞ እንደገጠማቸው ተሰምቷል፤ ይህንኑ የሚያሳዩ ቪዲዮዎችም በማኅበራዊ መገናኛ ብዙሃን ተሰራጭተዋል። ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር በተቃራኒ በቅርቡ ስብሰባ ያካሄደው ህወሃት አቶ ጌታቸው ረዳን ጨምሮ የተወሰኑ የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትን ማገዱን ይፋ አድርጓል። አቶ ጌታቸውም ህወሃት የክልሉን ጊዜያዊ አስተዳደር ከሥልጣን ለማውረድ እየሠራ ነው በማለት ከሰዋል። የትግራይ ፖለቲካዊ ኃይሎች እያሳዩት ነው ያሉትን በመኮነን በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች የችግሩ መነሻ ፖለቲካዊ በመሆኑ መፍትሄው አካታች ፖለቲካዊ መድረክ እንደሆነ አሳስበዋል። በዚህ መሀል ዛሬም የክልሉ ኅብረተሰብ በርካታ ችግሮች ትኩረት ያጡ መስለዋል። የትግራይ ክልል የፖለቲካ ሁኔታው ወዴት እያመራ ነው? 

ሚሊየን ኃይለ ሥላሴ
ሸዋዬ ለገሠ
ፀሐይ ጫኔ