በመተከል ዞን የተቀሰቀሰ ግጭት
ሐሙስ፣ ነሐሴ 6 2013ማስታወቂያ
በመተከል ዞን ማንዱራ ወረዳ ውስጥ ከትናንት በስቲያ ማክሰኞ አንድ ምግብ ቤት ውስጥ ተጀመረ በተባለው አለመግባባት በተቀሰቀሰ ግጭት ምክንያት የስድስት ሰዎች ህይወት ማለፉን ነዋሪዎቹ ተናግረዋል። ሁለት ሚኒባሶች በታጣቂዎች በዕለቱ መቃጠላቸውን እና በሚኒባሱ ውስጥ የነበሩ ሰዎች ላይም ጉዳት መድረሰን ነዋሪዎቹ ገልጸዋል። ዶቼቬለ የጉዳቱን መጠን ከአካባቢው ኮማንድ ፖስት በስልክ ለማረጋገጥ ያደረገው ጥረት ስልክ ባለማንሳታቸው አልተሳካም። መተከል ዞን የኮሙኒኬሽን መምሪያ በማህበራዊ ትስስር ገጹ«በግልገል በለስ ከተማና ቀጠናው ለጥፋት እና ለብጥብጥ ተሰማርተው የሚገኙ አካላትን ሁሉም በየአካባቢው በመቀናጀት መመከት አለበት» ሲል አሳስቧል። በከተማዋ እና አካባቢዋ የጠላት አጀንዳ ይዘው የሚንቀሳቀሱ ያላቸውን ኃይሎችን በመከታተል «በቁጥጥር ስር እንድታውሉ» በማለትም ጥሪ አቅርቧል።
ነጋሳ ደሳለኝ
ኂሩት መለሰ
ማንተጋፍቶት ስለሺ