1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በቄለም ወለጋ ተፈጽሟል ስለተባለው ግድያ የባለስልጣናት መልስ

ሰኞ፣ የካቲት 7 2014

የጊዳሚ ወረዳን ከወራት በኋላ ከታጣቂዎች ማስለቀቅ ቢቻልም በአንድ የአይን እማኝ የተረጋገጠውን የሰዎች መሞት የፀጥታ አካላት አሁንም አልደረሱበትም እንደ ሃላፊው፡፡ከጊዳሚ ወረዳ እና ከአጎራባች የምዕራብ ወለጋ ዞን ወረዳዎች ከ160 በላይ የመንግስት ሰራተኞች ኃላፊዎችና ነዋሪዎች ተወስደው እስካሁን ደብዛቸው መጥፋቱ በውል የተረጋገጠ ነው ብለዋል፡፡

https://p.dw.com/p/470F8
Äthiopien | Straßenszene in Menge Woreda
ምስል Negassa Dessalgen/DW

በኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ ዞን ጊዳሚ ወረዳ በጅምላ አንድ ቦታ ተገድለዋል የተባሉት 87 ሰዎችን ጨምሮ በታጣቂዎች ታፍነው የተወሰዱት 168 ሰዎች እስካሁን ይሙቱ ይኑሩ እንዳልታወቀ ባለስልጣናት ገለጹ፡፡ አስተያየታቸውን ለዶይቼ ቬለ የሰጡት የዞኑ ኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ እንዳሉት የጊዳሚ ወረዳን ከወራት በኋላ ከታጣቂዎች ማስለቀቅ ቢቻልም በአንድ የአይን እማኝ የተረጋገጠውን የሰዎች መሞት የፀጥታ አካላት አሁንም አልደረሱበትም፡፡ከቄለም ወለጋው ዞን ጊዳሚ ወረዳ እና ከአጎራባች የምዕረብ ወለጋ ዞን ወረዳዎች ከ160 በላይ የመንግስት ሰራተኞች፣ ኃላፊዎች እና ነዋሪዎች ተወስደው እስካሁን ደብዛቸው መጥፋቱ ግን በውል የተረጋገጠ ነው ብለዋል፡፡ታፍነው ከተወሰዱት ተጠቂዎች ጋር የነበረና ቆስሎ ካመለጠ ሰው ተገኘ በተባለው መረጃ መሰረት ግን ታፍነው የተወሰዱት 168 ሰዎች ተገድለዋል፡፡
 
ስዩም ጌቱ 
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ