1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በትግራይ ጦርነት የደረሱ የወሲብ ጥቃቶች

ሰኞ፣ መጋቢት 11 2015

ከአራት ወራት በፊት በኢትዮጵያ መንግስት እና በትግራይ አመራሮች መካከል የሰላም ስምምነት ቢፈረምም በሴቶች እና ልጃገረዶች ላይ በትግራይ ክልል የሚደርሰው የወሲብ ጥቃት አሁንም እንደቀጠለነው ተባለ። የኢትዮጵያ መንግስት ቃል አቀባይ ለገሰ ቱሉ በዚህ ዘገባ ላይ አስተያየታቸውን እና ምላሻቸውን ለማካተት የተደረገው ጥረት አልተሳካም።

https://p.dw.com/p/4OxEj
Äthiopien Frauen, die unter dem Konflikt um Tigray leiden
በትግራይ ክልል አሁንም የሴቶች መደፈር አለ ተባለ ምስል EDUARDO SOTERAS/AFP via Getty Images

ተጠያቂነት መስፈን አለበት 

የኢትዮጵያ መንግስት እና ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ጋር እርቅ በፈፀሙበት ቀን የ16 ዓመቷ ሀዳስ በትግራይ ክልል አድዋ ከተማ አቅራቢያ በሚገኝ መኖሪያ መንደሯ ምን እንደገጠማት ለዶቼ ቬሌ  አብራርታለች ። ለደህንነቷ ሲባል ስሟ የተቀየረላት ሀዳስ  ህዳር 23 ቀን 2015 ከእናቷ ጋር በመኖሪያ ቤታቸው ባሉበት ወቅት የመኖሪያ ቤታቸው በር በኃይል እንደተንኳኳ እና ስትከፍት ሁለት የኢትዮጵያ መከላከያ  ሰራዊቶች  እንደነበሩ  ስለሁኔታው አስረድታለች።

«አንዱ ብቻውን ወደ ቤት ገባ። በእጁ እንጨት ይዞ ነበር ሌላ ወታደር ሽጉጥ ይዞ ውጭ በር ላይ እየጠበቀ ነበር ወደ ጫካ ሊወስደኝ ቢሞክርም እምቢ አልኩ ቢላዋ እና ሽጉጥ እንዳለው ነገረኝ ከዛም በያዘው ዱላ ደበደበኝ።»

ሰዎች  ከጥቃት እንዲያስጥሏት በማሰብ የድረሱልኝ ድምጽ አውጥታ መጮህ ጀመረች። የሀዳስ የድረሱልኝ ድምፅ የሰሙ  ጎረቤቶች ወደ መኖሪያ ቤቷ ሊያድኗት ቢመጡም  ወታደሮቹ ስላስፈታሯቸው ምንም ሳያደርጉ ወደቤታቸው ተመልሰዋል።

«እድሜዬ ስንት እንደሆነ ሲጠይቀኝ አስራ አራት አመቴ ነው አልኩት አንቺ ውሸታም ነሽ አለኝ ጡት የለሽም ብሎ ጠየቀኝ ከዛ እናቴ ማልቀስ ጀመረች»

 ለሰዓታት በተደጋጋሚ  እንደደፈራት የተናገረችው ሀዳስ ብዙ ደም ስለፈሰሳት ወታደሮቹ  ከሄዱ በኋላ በአቅራቢያው ወደሚገኝ የህክምና አገልግሉት መስጫ አመራች። በህክምና መስጫው በአቅርቦት እጥረት ምክንያት መሰረታዊ እንክብካቤ  አገልግሎት ብቻ አግኝታ መመለሷን  ሃዳስ ተናግሯለች።

Äthiopien | Sexuelle Gewalt
የሰላም ስምነቱበተፈረመ በት ቀን በወታደር የተደፈረችው የ16 ዓመት ታደጊ ምስል privat

ሀዳስ በዛን እለት የደረሰባት ሰቆቃ እስካሁን አለቀቃትም። የስነ ልቦና እርዳታ ትፈልጋለች። በእርሷ ላይ ይህን ያደረሰባት ሰው ለፍርድ እንዲቀርብ ትፈልጋለች።

«በህግ ተጠያቂ መሆን አለበት በእኔ ላይ ብቻ ጥቃት ያደረሰው ሳይሆን  ሌሎችም ላይ የወሲብ ጥቃት የፈፀሙ  በሙሉ በህግ መጠየቅ አለባቸው።»

የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ባደረጓቸው ምርመራዎች የኢትዮጵያ ወታደሮች አጋሮቻቸው የኤርትራ ጦር ሰራዊት አባላት እና ሚሊሻዎች ወሲባዊ ጥቃቶች፣ አስገድዶ መድፈር፣ የቡድን አስገድዶ መድፈር እና ሌሎች የጾታ ጥቃቶች እንደተፈፀሙ ይፋ አድርገዋል።

Äthiopien | Krankenhaus in Mekelle
በትግራይ ለሁለት አመታት በተካሄደው ጦርነት ከ500 በላይ የአስገድዶ መድፈር ተጎጂዎች በመቀሌ አጠቃላይ ሆስፒታል ህክምና ተደርጎላቸዋልምስል privat

በበትግራይ የሚገኙ የህክምና ባለሙያዎች  በርካታ የመደፈር ጥቃቶች ሪፖርት ሳይደረጉ መቅረታቸውን ለዶቼ ቬሌ ተናግረዋል። አስገድዶ መድፈር እና ሌሎች ጾታዊ ጥቃቶች የሰላም ስምምነቱ ከተፈረመ በኋላ እንደቀጠሉ መሆናቸውን የጤና ባለሙያዎች ለዶይቼ ቬለ አረጋግጠዋል።

የመቀሌ ጠቅላላ ሆስፒታል ዳሬክተር ዶ/ር ፊሊሞን መስፍን ዶቼ ቬሌ እንደተናገሩት በግጭቱ ወቅት እርሳቸውና ባልደረቦቻቸው ለህብረተሰቡ እንክብካቤ ለማድረግ ስንቸገር ነበር ብለዋል

«ምንም አይነት የድንገተኛ መድኃኒት ወይም እንደ ደም ግፊት፣ ስኳር በሽታ፣ ኤች አይ ቪ እና የአዕምሮ ህመም ለመሳሰሉ ብርቱ በሽታዎች የሚሆኑ ምንም አይነት መድኃኒቶች የሉንም። ሁሉም አልቀዋል።  እነዚህ ታካሚዎች ከሚያስፈልጋቸውን መድሃኒት 10% ወይም 20% ብቻ ነው መስጠት የምንችለው።»

 አብዛኞቹን ታካሚዎች የመድሀኒት እጥረት እንዳለባቸው የገለጹት ዶክተር ፊልሞን  እራሳቸውን  ጨምሮ የሙያ ባልደረቦቻቸው ሊያደርጉት የሚችሉት ታካሚዎች አስፈላጊውን መድሃኒት ሌላ ቦታ ማግኘት እንደሚችሉ ተስፋ በመስጠት የሐኪም ማዘዣ መፃፍ ነው።

«ስምምነቱ ከተፈረመ አራት ወራት ሆኖታል። መድሀኒቶች እስከ አሁን ይቀርባሉ ብዬ እየጠበኩ ነበር እነዚህ ታካሚዎች ግን መጠበቅ አይችሉም። በየቀኑ እየሞቱ ነው።»

Äthiopien | Krankenhausdirektor, Dr. Mesfin in Mekelle
የመቀሌ ጠቅላላ ሆስፒታል ዳሬክተር ዶ/ር ፊሊሞን መስፍን ምስል privat

 በግጭቱ ወቅት ላለፉት ሁለት ዓመታት ከባልደረቦቻቸው ጋር  ከ500 በላይ የወሲብ ጥቃት የደረሰባቸውን ተጎጂዎች ማገዛቸውን የተናገሩት ዶክተር ፊልሞን እንደ ህክምና ባለሙያ እነዚህ ሴቶች  ያጋጠሟቸውን ነገሮች ማየት በጣም አስቸጋሪ ነበር ብለዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት ቃል አቀባይ ለገሰ ቱሉ  በዚህ ዘገባ ላይ አስተያየታቸውን እና ምላሻቸውን  ለማካተት የተደረገው ጥረት  አልተሳካም።

የኤርትራ የማስታወቂያ ሚንስትር የማነ መስቀል ለዶቼ ቬሌ በሰጡት ምላሽ በትግራይ የሚገኙ የኤርትራ ወታደሮች አደረሱት የተባለውን ጉዳት አስተባብለዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት እና ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት)  መካከል ለሁለት ዓመት በዘለቀው የእርስ በእርስ ጦርነት በግምት 600 ሺህ ሰዎች ተገድለዋል፤ በሚሊዮኖች ተፈናቅለዋል።

ማኅሌት ፋሲል 

እሸቴ በቀለ