1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በአማራ ክልል ውጊያ የቀጠለባቸው አካባቢዎች

ዓርብ፣ ነሐሴ 12 2015

በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ደንበጫ ከተማ በመከላከያ ሠራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ውጊያ መቀጠሉ እየተነገረ ነው። በምሥራቅ ጎጃም ዞን አማኑኤል ከተማም እንዲሁ ትናንት ከቀትር በኋላ በሁለቱ ኃይሎች መካከል ውጊያ እንደነበር፤ ዛሬ ጠዋትም እንዲሁ የተኩስ ልውውጦች እንደነበሩ ከነዋሪዎች ለመረዳት ተችሏል።

https://p.dw.com/p/4VKHs
ጎንደር ከተማ፤ ፎቶ ከማኅደር
ሰሞኑን አንጻራዊ መረጋጋት በታየባቸው ባሕር ዳር፣ ጎንደር፣ ደሴ እና ደብረ ብርሃን ከተሞች ዛሬም ተመሳሳይ ሁኔታ መኖሩ ነው የተሰማው። ፎቶ ከማኅደርምስል Alemnew Mekonnen/DW

የአማራ ክልል የጸጥታ ሁኔታ

በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ደንበጫ ከተማ በመከላከያ ሠራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ውጊያ መቀጠሉ እየተነገረ ነው። ዶቼ ቬለ መረጃውን እስካጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ጦርነቱ በመቀጠሉ ስለደረሰው ጉዳት መረጃ ከኗሪዎች ለማግኘት አልተቻለም። በምሥራቅ ጎጃም ዞን አማኑኤል ከተማም እንዲሁ ትናንት ከቀትር በኋላ በሁለቱ ኃይሎች መካከል ውጊያ እንደነበር፤ ዛሬ ጠዋትም እንዲሁ የተኩስ ልውውጦች እንደነበሩ ከነዋሪዎች ለመረዳት ተችሏል። የደብረ ማርቆስከተማ በመከላከያ ቁጥጥር ስር ከሆነ ቆየት ማለቱን የሚገልጹት ከተማዋ ነዋሪዎች መሠረታዊ አገልግሎቶች ግን በተሟላ ሁኔታ ሥራ እንዳልጀመሩ ነው የተሰማው። እንዲያም ሆኖ የባንክ አገልግሎት ሥራ መጀመሩን፤ ከደጀን ወደ ማርቆስ እና ከማርቆስ ወደ ደጀን መጓጓዣ መኖሩን፤ ሆኖም ግን በከተማዋ የመጓጓዣ አገልግሎት እንዳልተጀመረ ከነዋሪዎቹ የተገኘ መረጃ ያመለክታል። ሰሞኑን አንጻራዊ መረጋጋት በታየባቸው ባሕር ዳር፣ ጎንደር፣ ደሴ እና ደብረ ብርሃን ከተሞች ዛሬም ተመሳሳይ ሁኔታ መኖሩ ነው የተሰማው።  መደብሮች፣ የአገልግሎች መስጪያ ተቋማት፣ የመጓጓዣ አገልግሎትም ወደነበረበት እየተመለሰ ነዉ። ይሁንና ነዋሪዎቹ እንደሚሉት በግጭቱ ምክንያት የሰዎች እና የሸቀጦች ዝውውር እና አቅርቦት ተቋርጦ ስለነበር በአብዛኛዉ አካባቢ በተለይ የምግብ ሸቀጦች ዋጋ ሲበዛ ጨምሯል። በተለያዩ ከተሞች ሕዝባዊ ውይይቶች በመካሄድ ላይ መሆናቸውንም ከየአካባቢው ነዋሪዎችን ያነጋገረው ዘጋቢያችን ያገኘው መረጃ ያስረዳል። የየከተሞቹ ነዋሪዎችም ከሥጋትና ዉጥረት አልተላቀቁም።በአማራ ክልል ግጭቱ ከተቀሰቀሰበት ካለፈዉ ሐምሌ ማብቂያ ጀምሮ የኢንተርኔት አገልግሎት በመቋረጡ ከየአካባቢዉ መረጃ ማግኘትና የተገኘዉን መረጃ ማረጋገጥ በጣም እየከበደ ነዉ።

ፎቶ ከማኅደር፤ ባሕር ዳር ከተማ
መደብሮች፣ የአገልግሎች መስጪያ ተቋማት፣ የመጓጓዣ አገልግሎትም ወደነበረበት እየተመለሰ ነዉ። ይሁንና ነዋሪዎቹ እንደሚሉት በግጭቱ ምክንያት የሰዎች እና የሸቀጦች ዝውውር እና አቅርቦት ተቋርጦ ስለነበር በአብዛኛዉ አካባቢ በተለይ የምግብ ሸቀጦች ዋጋ ሲበዛ ጨምሯል። ፎቶ ከማኅደር፤ ባሕር ዳር ከተማ ምስል Alemnew Mekonnen/DW

ዓለምነው መኮንን

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ