1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በአማራ ክልል በጦርነት ምክንያት የተፈናቀሉት ወገኖች ለረሃብ መጋለጥ

ዓርብ፣ ነሐሴ 28 2013

በክልሉ ከ700 ሺህ በላይ በምግብ ለሥራ የሚተዳደሩ ወገኖች መኖራቸው ተገልጿል። በአማራ ክልል በአጠቃላይ ከአንድ ሚሊዮን 300ሺህ በላይ የዕለት ምግብ ርዳታ የሚፈልጉ ወገኖች እንደሚኖሩ ነው የተገለጸው። 

https://p.dw.com/p/3zszq
Sekota Stadt
ምስል DW/A. Mekonnen

በአማራ ክልል ህወሓት በተቆጣጠራቸው የምግብ ለሥራ ተጠቃሚ አካባቢዎች ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ፈጥኖ የርዳታ እህል የሚያደርስ ካልሆነ ከፍተኛ የርሀብ አደጋና ተያያዥ ችግሮች ሊከሰቱ እንደሚችሉ በአካባቢዎቹ የሚገኙ ነዋሪዎችና ተፈናቃዮች አመለከቱ። በክልሉ ከ700 ሺህ በላይ በምግብ ለሥራ የሚተዳደሩ ወገኖች መኖራቸው ተገልጿል። በአማራ ክልል በአጠቃላይ ከአንድ ሚሊዮን 300ሺህ በላይ የዕለት ምግብ ርዳታ የሚፈልጉ ወገኖች እንደሚኖሩ ነው የተገለጸው። በተለይም በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር፣ በሰሜን ወሎና ሰሜን ጎንደር አንዳንድ አካባቢዎች አብዛኛው ነዋሪ ሕይወቱን በምግብ ለሥራ የሚመራ መሆኑን ከባሕር ዳር ዓለምነው መኮንን ያለከው ዜና ያመለክታል።  

ዓለምነው መኮንን

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ