1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በአማራ ክልል አንድ ዓመት ባስቆጠረው ጦርነት ነዋሪዎች ምን አሉ ?

እሑድ፣ ነሐሴ 12 2016

ጦርነቱ ውድ የሆነውን የሰው ልጅ ህይወት ቀጥፏል፣ የብዙዎችን ኑሮ አመሰቃቅሏልም ብለዋል፣ አንድ ማንነታቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የባህር ዳር ከተማ ነዋሪ “የተሻለ ገቢ ያላቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ከተማዋን እየለቀቁ ወደ ሌሎች አካባቢዎች ሄደዋል” ነው ያሉት፡፡

https://p.dw.com/p/4jPlC
Äthiopien | Kämpfer der Fano-Miliz in Lalibela in der nördlichen Amhara-Region
ምስል Solan Kolli/AFP/Getty Images

አንድ ዓመት ያስቆጠረው የአማራ ክልል ጦርነት ያስከተለው ጉዳት

በአማራ ክልል ከአንድ ዓመት በላይ ያስቆጠረው ጦርነት  በክልሉ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና የሰዎች ግንኙነት ላይ ከፍተኛ ቀውስ መፍጠሩን ለዶቼ ቬሌ አስተያየታቸውን የገለጡ ነዋሪዎች አመልክተዋል፡፡ ጦርነቱ ውድ የሆነውን የሰው ልጅ ህይወት ቀጥፏል፣ የብዙዎችን ኑሮ አመሰቃቅሏልም ብለዋል፣ አንድ ማንነታቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የባህር ዳር ከተማ ነዋሪ “የተሻለ ገቢ ያላቸው  የከተማዋ ነዋሪዎች ከተማዋን እየለቀቁ ወደ ሌሎች አካባቢዎች ሄደዋል” ነው ያሉት፡፡ በጦርነቱ ምክንያት ሸቀጦች እንደልብ መዘዋወር ባለመቻላቸውና የሸቀጦች ዋጋም በእጅጉ በማሻቀቡ አብዛኛው ህብረተሰብ የእለት ኑሮውን መምራት እንዳልቻለም ገልጠዋል፡።

በአማራ ክልል የቀጠለዉ ዉግያ

ያነጋገርናቸው በምዕራብ ጎንደር፣ የምስራቅ ጎጃም፣ የምዕራብ ጎጃምና የደሴ ከተማ አስተዳደር ነዋሪዎች ጦርነቱ ያስከተለውን ጉዳትና በቀጣይr ሊሆን ይችላል ያሉትን ተስፋቸውን ለዶቼ ቬሌ ተናግረዋል፡፡

ዓለምነው መኮንን

ታምራት ዲንሳ

ኂሩት መለሰ