በአማራ ክልል የተደነገገው አዋጅና የክልሉ የፀጥታ ሁኔታ
ዓርብ፣ ሐምሌ 28 2015ማስታወቂያ
በዓለም ዜና እንደተከታተላችሁት ዛሬ የአስቸኳይ ጉዜ አዋጅ በተደነገገበት በአማራ ክልል ርዕሰ ከተማ ባህርዳር በሁለት አካባቢዎች ቦምብ ፈንድቷል። ፍንዳታው ስላደረሰው ጉዳት ዝርዝር መረጃ እንዳልወጣ የባህርዳሩ ወኪላችን አለምነው መኮንን እስቱድዮ ልንገባ ስንል ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት አሳውቆናል። ከዚያ ቀደም ሲል አለምነው ባህርዳር ሰላማዊ እንደሆነች ነበር የነገረን ። በሌሎች የአማራ ክልል ከተሞች ግን ዛሬም ግጭቶች እንደነበሩ ገልጿል።ስለ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁም የክልሉ ህዝብ የተለያዩ አመለካከቶች እንዳሉትም ተናግሯል።
አለምነው መኮንን
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ