በአማራ ክልል የትምርት ጥራት መጓደል
ሐሙስ፣ ኅዳር 6 2011ማስታወቂያ
በአማራ ክልል በትምህርቱ ዘርፍ የሚታዩ ችግሮች ለትምህርት ጥራት ማሽቆልቆል አይነተኛ ምክንያት መሆናቸውን ወላጆች፣ መምህራንና ተማሪዎች አመለከቱ፡፡ እንደ አስተያየት ሰጪዎች አራተኛ ክፍል ደርሰው ስማቸውን ማጻፍ የማይችሉ ተማሪዎች ቁጥር ቀላል አይደለም። የመምህራንና የመፀሐፍትእጥረት፣የመምህራንና የወላጆች ጥምረት መላላት የቁጥጥርና ክትትል አለመኖር፣ የቤተሙከራ ኬሚካሎች እጥረት፣ የመምሕራን የጊዜ አጠቃቀም ችግርና ሌሎችም ተግዳሮቶች ለትምህርት ጥራት መጓደል ዋና ዋና ምክንቶች ናቸው፡፡ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ በበኩሉ የተጠቀሱ ችግሮች አብዛኛዎቹ ትክክል መሆናቸውን ያምናል፤ የቢሮው ኃላፊ ዶ/ር ይልቃል ከፍአለ እንደሚሉት ችግሮችን ለማስወገድና የትምህርት ጥራትን ለማምጣት ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት ይሰራል ብለዋል፡፡
አለምነዉ መኮንን
አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሐመድ