በአዲስ አበባ ፒያሳ አከባቢ በቤቶች ፈረሳ መውደቂያ አጣን ያሉ ነዋሪዎች
ረቡዕ፣ መጋቢት 6 2015ማስታወቂያ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፒያሳ አከባቢ ከራስ መኮንን ድልድይ ጀምሮ በተለምዶ እሪ በከንቱ እስከሚባለው ሰፈር ሰሞኑን የሚከናወነው የቤቶች ፈረሳ በርካቶቻችንን ደጅ ያስቀረን ነው ሲሉ ቅሬታ አቅራቢዎች ገለጹ። ከአከባቢው የመሬት ይዞታ ያላቸው እና በብዛት የቀበሌ ቤት ውስጥ ይኖሩ የነበሩ ነዋሪዎች ካሣ ተሰጥቷቸው እንዲሁም የጋራ መኖሪያ ቤቶች እና ምትክ የቀበሌ ቤቶች መሰጠታቸውን ያልሸሸጉት ቅሬታ አቅራቢዎቹ በጥገኝነት እና በተለያየ መንገድ ለዓመታት በዚያ የኖርን ግን መፍትሄ ተነፍገናል ይላሉ። ለደህንነታቸው ሲባል ስማችን አይጠቀስ ብለው አስተያየታቸውን ለዶቼ ቬለ የገለጹ ተፈናቃይ ነዋሪዎቹ፤ ለዓመታት እዚያው ሕይወት መሥርተውና ልጅ ወልደው በማስተማር ላይ መሆናቸውን በማመልከት መንግሥት ለኛም መፍትሄ ሊያበጅልን ይገባልም ብለዋል። የተጠቀሰው አካባቢው እንጦጦ ፓርክን እንደ ሸገር ፕሮጀክት ካሉቱ የወንዝ ዳር ልማት ጋር ለማገናኘት እየተሠራበት መሆኑን ቀደም ሲል መንግሥት እቅዱን በተደጋጋሚ ማሳወቁ ይታወሳል።
ሥዩም ጌቱ
ሸዋዬ ለገሠ
አዜብ ታደሰ