1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ተዘርፈው የነበሩ ጥንታዊ የኢትዮጵያ ቅርሶች ተመለሱ

ቅዳሜ፣ ኅዳር 11 2014

ከ150 ዓመታት በፊት ከመቅደላ ተዘርፈው የተወሰዱ 13 ታሪካዊና ሃይማኖታዊ ቅርሶች ከለንደን ዛሬ ወደ አዲስ አበባ ተመልሷል። ቅርሶቹ በግለሰቦች እጅ የነበሩ እና በጨረታ ከመሸጣቸው በፊት በለንደን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ፣ የኢትዮጵያ ቅርስ አስመላሽ ግብረ ኃይል እና ሼሄራዛድ ፋውንዴሽን ከተባለ ድርጅት ጋር በመተባበር እንዲመለሱ የተደረጉ ናቸው።

https://p.dw.com/p/43HpZ
Precious artefacts looted by British soldiers returned to Ethiopia
ምስል Solomon Muchie/DW

በእንግሊዞች ተዘርፈው የነበሩ ጥንታዊ ቅርሶች ተመለሱ

ከ150 ዐመታት በፊት ከመቅደላ ተዘርፈው የተወሰዱ 13 ታሪካዊና ሃይማኖታዊ ቅርሶች ከለንደን ዛሬ ወደ አዲስ አበባ ተመልሷል።

ቅርሶቹ በግለሰቦች እጅ ላይ የነበሩ እና ለጨረታ ቀርበው ከመሸጣቸው በፊት በለንደን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ፣ የኢትዮጵያ ቅርስ አስመላሽ ግብረ ኃይል እና ለኢትዮጵያ ተቆርቃሪ ግለሰቦች ሼሄራዛድ ፋውንዴሽን ከተባለ ድርጅት ጋር በመተባበር እንዲመለሱ የተደረጉ ናቸው።

በለንደን የኢትዮጵያ ኤምባሲ በቀጣይ በግለሰቦች እጅ ከሚገኙ ጥንታዊ የኢትዮጵያ ቅርሶች በተጨማሪ በብሪታኒያ ሙዚየም ውስጥ የሚገኙ 12 ፅላቶችን ለማስመለስ ሥራ እንደተጀመረና በቅርቡም የመመለስ ተስፋ እንዳለ ተናግሯል።

የቱሪዝም ሚኒስቴር ቅርሶቹ ጥበቃ ተደርጎላቸው ለሕዝብ እይታ ይቀርባሉ ብሏል።

እነዚህን ቅርሶች ለኢትዮጵያ ያስረከበው ሼሄራዛድ ፋውንዴሽን ቅርሶቹን ለመግዛት ምን ያህል ወጪ እንዳወጣ እንደማይታወቅ ተነግሯል።

ሰለሞን ሙጬ

ታምራት ዲንሳ