1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በዓለማችን የሞት ቅጣት ፍርድ ጨመረ

ሐሙስ፣ ግንቦት 10 2015

ባለፈዉ የጎርጎረሳዉያን 2022 ዓመት በዓለም ዙሪያ የታየዉ የሞት ቅጣት ቁጥር ከዓለፉት አምስት ዓመታት ጋር ሲነጻፀር ከፍተኛ ነዉ ሲል ዓለም አአፉ የሰብዓዊ መብቶች ተከራካሪ ድርጅት አስታወቀ። በአንድ ዓመት ብቻ በ 20 ሃገራት ዉስጥ 883 ሰዎች በሞት ቅጣት ተገድለዋል፤ በኢራን ብቻ 576 ሰዎች የሞት ቅጣት ተፈፅሞባቸዋል።

https://p.dw.com/p/4RSNw
Iran Todesurteil Hinrichtung
ምስል Christoph Hardt/Geisler-Fotopress/picture alliance

ባለፈዉ የጎርጎረሳዉያን 2022 ዓመት በዓለም ዙሪያ የታየዉ የሞት ቅጣት ቁጥር ከዓለፉት አምስት ዓመታት ከታየዉ ሁሉ ከፍተኛዉ መሆኑን ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ተከራካሪ ድርጅት አምስቲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ። ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ተከራካሪ ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል ዛሬ ይፋ ባደደረገዉ ዓመታዊ መግለጫ በ 20 ሀገራት ቢያንስ 883 ሰዎች የሞት ቅጣት ብይን ተፈጽሞባቸዋል። ባለፈዉ ዓመት  በኢራን 576 ሰዎች በስቅላት ተገድለዋል።  በሳዉዲ ዓረቢያ 196 ሰዎች፤  በግብፅ 24 ሰዎች እንዲሁም በዩናይትድ ስቴትስ 18 ሰዎች የሞት ቅጣት ተፈፅሞባቸዉዋል። ባለፈዉ ዓመት በሳዉዲ አረብያ 196 ሰዎች የሞት ቅጣት ተፈጽሞባቸዋል፤ ይህ ከፍተና የሞት ቅጣት ቁጥር በሳዉዲአረብያ ሲታይ  ከ 30 ዓመት ወዲህ ከፍተኛዉ ነዉ ተብሏል። ከዚህ ሌላ በከፍተኛ ሚስጢር የሞት ቅጣት በሚፈፀምባቸዉ በቻይና፣ በሰሜን ኮሪያ እና በቪየትናም በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ላይ የሞት ቅጣት ፍርድ መፈፀሙን የሚሳዩ ነገሮች እንዳሉ የአምነስቲ ዘገባ ያመለክታል። ይሁንና አፍሪቃ ሪፐብሊክ፣ ኢኳቶሪያል ጊኒ፣ ካዛክስታን፣ ፓፑዋ ኒው ጊኒ፣ ሴራሊዮን እና ዛምቢያ  ባለፈው ዓመት የሞት ቅጣትን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የሻሩ አምስት ሃገራት ናቸዉ። በዚህም ምክንያት የሞት ቅጣትን ለማስቀረት  "የተስፋ ጭላንጭል" መታየቱን አምነስቲ በዘገባዉ ጠቅሷል።

 

አዜብ ታደሰ 

ኂሩት መለሰ