1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ወንጀልኢትዮጵያ

የደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች በጋምቤላ ያደረሱት ጥቃት

ሰኞ፣ ሚያዝያ 14 2016

በጋምቤላ ክልል አኙዋ ብሔረሰብ ዞን ጆር ወረዳ ውስጥ መጋቢት 26/2016 ዓ.ም ከደቡብ ሱዳን የመጡ ታጣቂዎችና በክልሉ ውስጥ የሚገኙ ጸረ ሰላም የተባሉ ሀይሎች በመተባበር ባደረሱት ጥቃት 738 ቤቶች መቃጠላቸው ተገለጸ፡፡

https://p.dw.com/p/4f3Gd
Äthiopien | Stadt Gambella
የጋምቤላ ክልል ጠረፋማ ከመሆኑ የተነሳ የድምበር ዘለል የታጣቂዎች ጥቃት በተደጋጋሚ ይከሰታልምስል Negassa Desalegn/DW

በወቅቱ በነበሩ ጥቃቶች የበርካታ ሰዎች ህይወት ማለፉን እና 14 ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን አንድ የክልሉ ባለስልጣን ተናግረዋል፡፡ የክልሉ የአደጋ ስጋት አመራር አገልግሎት እንዳስታወቀው ደግሞ በጆር ወረዳ ከተለያዩ ቀበሌዎች 6100 ሰዎች መፈናቀላቸውን አመልክተዋል፡፡ 

የጋምቤላ ክልል ጠረፋማ ከመሆኑ የተነሳ  የድምበር ዘለል የታጣቂዎች ጥቃት በተደጋጋሚ እንደምደርስበት የክልሉ መንግስት አመልክቷል፡፡ ከሁለት ሳምንት በፊት መጋቢት 26/2016 ዓ.ም በክልሉ አኙዋ ብሔረሰብ ዞን ጆር የተባለ ወረዳ ውስጥ ከደቡብ ሱዳን የመጡ የተባሉ ታጣቂዎች በአካባቢ ይንቀሳቀሳሉ የተባሉ ሌሎች ጸረ ሠላም ተብሎ የተሰሙ ሀይሎች ጥቃት ማድረሳቸው ተገልጸዋል፡፡ በደረሰው ጥቃትም ከተለያዩ የወረዳው አካባቢዎች  በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸውን የክልሉ የአደጋ ስጋት አመራር አገልግሎት ኃላፊ አቶ ጋት ቤል ሙን ለዶቸቨሌ ገልጸዋል፡፡ ለተፈናቀሉ ዜጎች የዕለት ደራሽ ድጋፍ እየቀረበላቸው እንደሚገኝ አቶ ጋትቤል ተናግረዋል፡፡ 

Äthiopien | Stadt Gambella
በጋምቤላ ከሁለት ሳምንት በፊት በደረሰው ጥቃት 61 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 14ቱ ደግሞ ቀስለዋል ምስል Negassa Desalegn/DW

ከሁለት ሳምንት በፊት በደረሰው ጥቃት 61 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 14ቱ ደግሞ ቀስለዋል 

በጆር ወረዳ በደረሰው ጥቃት በታጣቂዎች ታፍነው ከተወሰዱት 7 ህጻናት መካከል 2ቱ መመለሳቸው የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት አመልክቷል፡፡ አንድ ማንነታቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ የክልሉ ባስልጣን በሰጡን መረጃ በጆር በደረሰው ጥቃት ከደቡብ ሱዳን የተሻገሩ ታጣቂዎች እና በአካባቢው ይንቀሳቀሰሉ ያሏቸው ታጣቂ ቡድኖች በጥምረት ባደረሱት ጥቃት በርካታ ሰው ህይወት ማለፉን ገልጸዋል፡፡ በመቶዎች የሚቆጠሩ የቁም እንስሳትም በእነዚሁ ታጣቂዎች መወሰዳቸውን ባለስልጣኑ ገልጸዋል፡፡ 

በጋምቤላ ክልል በላማዊ ሰዎች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች መበራከት

በጋምቤላ ክልል በተደጋጋሚ በተከሰቱት የሠላም እጦት ጋር ተያይዙ የተጠረጠሩ 14 የክልሉ አመራሮችን  በቁጥጥር ስር ማዋሉን የክልሉ መንግስት ከሳምንት በፊት መግለጹ ይታወሳል፡፡ በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል ሁለቱ የዞን ከፍተኛ አመራሮቸ ሲሆኑ የተቀሩት ደግሞ የወረዳ አመራሮች ናቸው፡፡ በክልሉ ከፍተኛ ወድመት ያስከተለውን ግጭት ለማስቆም ኃላፊነታቸውን በአግባቡ አልተወጡም የተባሉት የክልሉን የሠላምና ጸጥታ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊን ጨምሮ አራት አመራሮች ከኃላፊነታቸው ማንሳቱ ተዘግበዋል፡፡ ባለፈው አርብ ሚያዚያ 11/2016 ዓ.ም በህዝቡ የሚነሱ የሰላምና ልማት ጥያቄዎችን ምላሽ ለመስጠት የክልሉ መንግስት 8 አዳድስ አመራሮችን መሾሙን አስታውቋል፡፡ 

ነጋሳ ደሳለኝ
ልደት አበበ
አዜብ ታደሰ