ብሔራዊ ምክክር፣ እርቅ ወይስ ፍትህን ማስፈን ይቅደም
እሑድ፣ ጥር 15 2014ማስታወቂያ
ኢትዮጵያ ከአንድ አሳሳቢ ጉዳይ ወደሌላው እየገባች ሕዝቧም የመንፈስም የአካልም እረፍት ካጣ በርካታ ዓመታት ተቆጥረዋል። በፖለቲካ ርዕዮተ ዓለም እና በብሔራዊ ጉዳዮች ለመግባባት ያዳገታቸው የሀገሪቱ ፖለቲከኞች ዘመናዊ አስተዳደር በማምጣት ሰበብ ለረዥም ዓመታት የተፋጩበት አካሄድ ስለጉዳዩ ምንም ያልተረዱ ዜጎችን ብዙ ዋጋ አስከፍሏል። በተለያዩ አጋጣሚዎች ስለብሔራዊ ምክክርም ሆነ ውይይት የተነሱ ሃሳቦች ወደጎን እየተገፉ ሃሳብ ተቀባይነት እንዲኖረው ኃይል የመጠቀሙ አካሄድ ዛሬም በሺህዎች የሚገመቱት ለሞት፤ በሚሊየን የሚቆጠሩት ለስቃይ እንግልት መዳረጉ ይታያል። በቅርቡ መንግሥት ለብሔራዊ ምክክር መዘጋጀቱን መግለጹ ብዙዎች እንደውም ዘግይቷል በሚል በአዎንታ ሲቀበሉት፤ በተካረረው ፖለቲካዊ አካሄድ ምክንያት በተከተለው ጦርነትም ሆነ ማንነትን መሰረት በማድረግ የተለያዩ ጊዜያት እና አካባቢዎች ሕይወታቸውን ያጡ፣ አካል እና ንብረታቸው የተጎዳ ወገኖች ፍትህ ካላገኙ ምኑን ሀገራዊ መግባባት መጣ በሚል የሚጠይቁ በርካታ ናቸው። ሙሉ ውይይቱን ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ።
ሸዋዬ ለገሠ