1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ቦረና ዉስጥ ከብት እያለቀ፣ ሰዉም እየተጠማ ነዉ

ረቡዕ፣ ጥር 18 2014

በድርቁ ክፉኛ በተጎዱት በሶማሌ ክልልና በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን በመቶ ሺሕ የሚቆጠሩ የቀንድ ከብቶችና እንስሳት መሞታቸዉን ባለስልጣናት አስታዉቀዋል። ባለሙያዎች እንደሚሉት ቦረና ዞን በድርቅ ከተመታ አንድ ዓመት ደፍኗል።ድርቁ በእንስሳት ላይ ካደረሰዉ ጉዳት በተጨማሪ ተማሪዎች ትምሕርት እያቋረጡ፣ነዋሪዎች ዉኃ በቁነና እየታደላቸዉ ነዉ።

https://p.dw.com/p/467Pe
Südostäthiopien | Dürre in Borena
ምስል Seyoum Getu/DW

እንስሳት እያለቁ ነዉ፣ከ6 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ለአደጋ ተጋልጧል

የምስራቅ፣ የደቡብ ምሥራቅና ደቡብ ኢትዮጵያን የመታዉ ድርቅ ከ6 ሚሊዮን የሚበልጥ ሕዝብ ለረሐብ ማጋለጡን የተለያዩ ድርጅቶችና ተቋማት እያስታወቁ ነዉ። በድርቁ ክፉኛ በተጎዱት በሶማሌ ክልልና በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን በመቶ ሺሕ የሚቆጠሩ የቀንድ ከብቶችና እንስሳት መሞታቸዉን ባለስልጣናት አስታዉቀዋል።ባለሙያዎች እንደሚሉት ቦረና ዞን በድርቅ ከተመታ አንድ ዓመት ደፍኗል።ድርቁ በእንስሳት ላይ ካደረሰዉ ጉዳት በተጨማሪ ተማሪዎች ትምሕርት እያቋረጡ፣ነዋሪዎች ዉኃ በቁነና እየታደላቸዉ ነዉ።የመንግሥት ባለስልጣናት ግን ድርቁ ያስከተለዉን አደጋ ለመቋቋም በቂ ዝግጅት ማድረጋቸዉን ይናገራሉ።«በቂ» የሚባለዉ ዝግጅት ምንነት ግን ግልፅ አይደለም።የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከ20 ሚሊዮን በላይ ኢትዮያዊ አስቸኳይ የምግብ ርዳታ እንደሚያስፈልገዉ ባለፈዉ ወር አስታዉቆ ነበር።

Äthiopien | Dürre in Borena
ምስል Firaol Wako/PHD

ስዩም ጌቱ 

ነጋሽ መሐመድ

እሸቴ በቀለ