ውዝግቦችየመካከለኛው ምሥራቅተዳፍኖ የቆየው የሶርያ የርስ በርስ ጦርነት ዳግም እያገረሸ ይሆን?To play this audio please enable JavaScript, and consider upgrading to a web browser that supports HTML5 videoውዝግቦችየመካከለኛው ምሥራቅEshete Bekele23 ኅዳር 2017ሰኞ፣ ኅዳር 23 2017የሶርያ አማጽያን በፕሬዝደንት በሺር አል አሳድ መንግሥት ላይ የከፈቱት ጥቃት ተዳፍኖ የቆየውን የርስ በርስ ጦርነት ዳግም እየቆሰቆሰው ይገኛል። አማጽያኑ አሌፖን ተቆጣጥረው ሐማ ወደ ተባለች ከተማ ሲገሰግሱ ሶርያ እና ሩሲያ በአየር ከፍተኛ ድብደባ እየፈጸሙ ነው። የአሳድ አጋር ሒዝቦላሕ አሁን ተዋጊዎች ወደ ሶርያ የመላክ ዕቅድ እንደሌለው አስታውቋል። የሶርያን ጉዳይ የቀጠናው ሀገራት እና ልዕለ ኃያላን በእግር ጥፍራቸው ቆመው እየተከታተሉ ነው። https://p.dw.com/p/4nezsማስታወቂያ