ችኩንጉንያ በፍጥነት መሠራጨቱ
ሐሙስ፣ ነሐሴ 23 2011ማስታወቂያ
በድሬዳዋ የተከሰተው ችኩንጉንያ የተባለው ወረርሽኝ 1 ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ16 ሽህ ሰዎችን ማጥቃቱን መንግስት አስታወቀ። ወረርሽኙ በከፍተኛ ፍጥነት ለመሠራጨቱ ምክንያት ነው የተባለውም የክረምቱ ዝናም ማየልና የሚያቁሩ ውሐዎች መብዛት ነው ሲል የኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በተለይ ለዶቼ ቬሌ DW ዛሬ ተናግሯል። ከወባ በሽታ ጋር ተመሳሳይ ምልክት ላለው ለዚህ ወረርሽኝ፣የመሰል በሽታዎች አስታጋሽ መድሐኒቶች እንጅ ራሱን የቻለ መድሃኒት እንደሌለውም ተገልጿል። ወረርሽኙ ከዚህ ቀደም በአፋር እና ሶማሌ ክልሎች ተከስቶ የነበር ቢሆንም እስካሁን በበሽታው የሰው ህይወት ስለመጥፋቱ ሪፖርት እንዳልደረሰው ተቋሙ አስታውቋል። የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ሰሎሞን ሙጬ ዝርዝር ዘገባ አለው።
ሰሎሞን ሙጬ
ኂሩት መለሰ
ተስፋለም ወልደየስ