ነዋሪዎቿን ሸኝታ ሌላ መልክ የያዘችው ካዛንቺስ/የምስል ዘገባ/
ካዛንቺስ ፒያሳ ላይ እንደሆነው ሁሉ ለተሻለ ልማት በሚል ከተማዋን ከተማ አድርገው የነበሩ ደሳሳ የመኖሪያ ቤቶች፣ ለዘመናት የሚታወቁና የቆዩ የንግድ እና የአገልግሎት መስጫ ተቋማት በትልልቅ ሕንፃዎች እየተተኩ ነው።ጎዳናውም ሰፍቶ ሌላ መልክ ይዟል።ካሳንችስ የተሟላ የከተማ ሕይወት መገለጫ እና የዘመናዊነት ምልክት ነበረች። አሁን ግን ፈርሳለች።
ካዘንቺስ የዓብያተ መንግሥታት የአለም አቀፍ ተቋማት አዋሳኝ ቦታ
ካዘንቺስ ዓብያተ መንግሥታት ማለትም የምኒሊክ ቤተ መንግሥት እና የታችኛእ የኢዮቤልዮ ዓብያተ መንግሥታት የሚያዋስኗት፣ ዓለም አቀፉ የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ግዙፍ ግቢ የሚገኝባት፣ ዕድሜ ጠገብ እና ቅንጡ ሆቴሎች የተመሠረቱባት ታሪክን ከአካባቢው ሰው ኑሮ አጣምራ ይዛ የቆየችም ናት።በኮሪደር ልማት መልሶ ማልማት የፈረሰችው ካዘንቺስ አሁን መልኳም ሁሉ ነገሯም ተለውጧል።
የእውቁ ኢትዮጵያዊ ደራሲ ዶክተር ከበደ ሚካኤል መኖሪያ ቤት አካባቢ
የእውቁ ኢትዮጵያዊ ደራሲ ዶክተር ከበደ ሚካኤል መኖሪያ ቤት አለፍ ብሎ የሚገኝ አካባቢ ነው። ባለ ቅኔ፣ ደራሲ፣ እና ዘርፈ ብዙ ሙያ ያላቸው ዶክተር ከበደ ሚካኤል በርካታ የሥነ ጽሑፍ ሥራዎችን ያዘጋጁ ሲሆን ታሪክና ምሳሌ፣ የሕሊና ብርሃን፣ የቅኔ ውበት፣ ጃፓን እንዴት ስለጠነች የሚሉትና ሌሎችም ሥራዎቻቸው ይገኛሉ።
የካሳንችሱ ሀናን ዳቦ፣ ዕድሜ ጠገቡ ኮፊ ዴይስ
ሀናን ዳቦ፣ ዕድሜ ጠገቡ ኮፊ ዴይስ እና ሐረር ቀስተ ደመና ባር ያሉበት መደዳ ጀርባ የሚገኝ ቦታ ነበር። እነዚህ ስፍራዎች ከኢንተር ኮንቲኔንታል ሆቴል ፊት ለፊት የሚገኙ ፣ የብዙ ሰዎች መገናኛ የነበሩ፣ ወደ መገናኛ የሚጓዙ ሰዎች ታክሲ የሚይዙባቸው እና አማካኝ መገናኛ ስፍራዎች ነበሩ።
ከመለስ ዜናዊ ፋውንዴሽን ፊት ለፊት የሚገኝ አካባቢ
በመለስ ዜናዊ ፋውንዴሽን ፊት ለፊት የሚገኝ አካባቢ ነው።በኮሪደር ልማት መልሶ ማልማት የፈረሰችው ካዘንቺስ አሁን መልካም ሁሉ ነገራም ተለውጧል።አነጋጋሪው የኮሪደር ልማት፣ በጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ ጠንከር ያለ ምክር አዲስ አበባን እየለወጠ ያለ ይመስላል። ለብስክሌቶች እና ለእግረኞች አዲስ መንገዶች እየተጨመሩ ሲሆን መንገዶቹም አዳዲስ መብራቶች ተጭነዋል። ህንጻዎች በአዲስ አበባ በአዲስ መልክ ቀለም በመቀባት ላይ ናቸው።ከአካባቢው ለተነሱ ድሆች ግን የተመቸ አይመስልም።
ጥንታዊው ቤት
ይህ በመለስ ዜናዊ ፋውንዴሽን እና በክቡር ዶክተር ከበደ ሚካኤል መኖሪያ ቤት መካከል የሚገኝ አሠራሩ የረጅም ዘመን ታሩክ እንዳለው የሚነገርለት ጥንታዊ ቤት ነው። እነዚህን መሰል እድሜ ጠገብ ህንፃዎች እየፈረሱ ህንጻዎች በአዲስ አበባ በአዲስ መልክ ቀለም በመቀባት ላይ ናቸው። የውሃ ምንጮች፣ አረንጓዴ ቦታዎች እና የመቀመጫ ቦታዎች የልማቱ አካል ናቸው።ይሁን እንጂ እነዚህ ማሻሻያዎች በኑሮ ውድነት ላይ የሚገኙትን የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ ላያደርጉ ይችላሉ። ነዋሪዎች የከተማዋን አዲስ ገጽታ ቢያደንቁም የኮሪደሩ ልማት ድሆችን እና መደበኛ ባልሆነው ኢኮኖሚ ውስጥ የተሳተፉትን የሚያፈናቅል ይመስላል።
ዳሽን ተራራ ሆቴል አካባቢ የሚገኝ ስፍራ
ይህ ቦታ የውጭ ጎብኝዎችን ጨምሮ ኢትዮጵያውያን በብዛት ይገለገሉበት የነበረው ታዋቂው ዳሽን ተራራ ሆቴል አካባቢ የሚገኝ ስፍራ ነው። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮሪደር ልማት ፕሮጄክቱን በቀጠለበት በአሁኑ ወቅት ከከተማዋ አንጋፋ ሰፈሮች አንዱ የሆነው ካዛንቺስ እንዳልነበረች ሆናለች።
መሃል ካዛንቺስ ከቶታል በስተቀኝ
መሃል ካዛንቺስ ከቶታል በስተቀኝ በኩል ያለው ሆቴሎችን፣ ኬፌዎችን፣ የኮምፒውተር ቤቶችን ፣ የመዝናኛ ክበቦችን እና ሌሎችንም በአንድ ጥቅጥቅ አድርጎ ይዞ የነበረው መንደር ነው። ይህ ሥፍራ ወደ ታላቁ የምኒልክ ቤተ መንግሥት በፈንድቃ የባህል ማዕከል አድርጎ፣ በአለም ቡና ወደ ላይ ከመውጣትዎ በፊት የሚገኘው መንደር ነው።
ከመለስ ዜናዊ ፋውንዴሽን አለፍ ብሎ የሚገኙ የአስፓልት ዳር ዕድሜ ጠገብ ቤቶች
ካዘንቺስ ዓብያተ መንግሥታት ማለትም የምኒሊክ ቤተ መንግሥት እና የታችኛእ የኢዮቤልዮ ዓብያተ መንግሥታት የሚያዋስኗት፣ ዓለም አቀፉ የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ግዙፍ ግቢ የሚገኝባት፣ ዕድሜ ጠገብ እና ቅንጡ ሆቴሎች የተመሠረቱባት ታሪክን ከአካባቢው ሰው ኑሮ አጣምራ ይዛ የቆየችም ናት።
ፈንድቃ የባህል ምሽት ቤት አካባቢ
ፈንድቃ የባህል ምሽት ቤት ሳይደርሱ ባለው የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ግቢ ፊት ለፊት የሚገኝ የነበረ ደማቅ መንደር የነበረበት ሥፍራ ነው።በካዛንቺስ ውስጥ የነበሩ ደማቅ ቡና ቤቶች፣ ካፌዎች እና ንግዶች አሁን የሉም።ካዛንቺስ ከመፍረሱ በፊት መንግስት እንደ ፒያሳ ያሉ ነባር የከተማዋ ሰፈሮች በተመሳሳይ ሁኔታ ፈርሰዋል።
ከሴቶች አደባባይ ፊት ለፊት ያለው የካዛንቺስ አካባቢ
ካዛንቺስ የዕለት ጉርስ ለማግኘት የግብርና ምርቶችን እንደ ሽንኩርት፣ድንች እና ጎመን ቸርችረው የሚያድሩትን፣ የታክሲ ሠራተኞችን፣ የሻሂ ቡና፣ በቆሎን ጨምሮ ለአፍ የሚሆን ትኩስ ምግብና መጠጡን፣ የመዝናኛ ስፍራውን አቅፋ የያዘችም ነበረች። በኮሪደር ልማት መልሶ ማልማት የፈረሰችው ካዘንቺስ አሁን መልኳም ሁሉ ነገሯም ተለውጧል።