1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ዲጂታል ዓለምዓለም አቀፍ

በአማራ ክልል የኢንተርኔ እገዳ እንዲነሳ ዓለም አቀፍ ጥሪ

ሐሙስ፣ ኅዳር 20 2016

በአማራ ክልል የተጣለው የኢንተርኔት እገዳ በአስቸኳይ እንዲነሳ ሲሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ተቆርቋሪዎች ጠየቁ ። ጥያቄውን ያቀረቡት ከ150 ሃገራት የተውጣጡ ወደ 300 የሚሆኑ ለሰብአዊ መብቶች መከበር የሚሟገቱ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ናቸው ።

https://p.dw.com/p/4ZcaY
በአማራ ክልል ኢንተርኔት እንደታገደ ነው
የፋኖ እና የመከላከያ ሠራዊት ጦርነት በቀጠለበት የአማራ ክልል ኢንተርኔ እገዳ ተጥሎበት ከተቋረጠ ወራት ተቆጥረዋል ምስል K. Nie/Design Pics/IMAGO

የኢንተርኔት እገዳ ርምጃ በኢትዮጵያ ከሌሎች ሃገራት ይበልጣል ተባለ

በአማራ ክልል የተጣለው የኢንተርኔት እገዳ በአስቸኳይ እንዲነሳ ሲሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ተቆርቋሪዎች ጠየቁ ። ጥያቄውን ያቀረቡት ከ150 ሃገራት የተውጣጡ ወደ 300 የሚሆኑ ለሰብአዊ መብቶች መከበር የሚሟገቱ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ናቸው ። የእገዳ ተግባሩ ከሌሎች የአፍሪቃ ሃገራት በኢትዮጵያ የከፋ መሆኑ ተገልጿል ። እገዳውን በማውገዝም (Access Now) እና (#KeepItOn coalition) የተባሉ ሁለት ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ግልጽ ደብዳቤ ከጻፉ ወራት ተቆጥረዋል ። የኢንርኔት እገዳው ግን እንደቀጠለ ነው ።  

«…በአማራ ክልል ላይ የተጣለውን የኢንተርኔት እገዳአለ-አንዳች ማንገራገር፣ መስመሮቹን በአስቸኳይ እንዲከፍቱ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን አህመድን እንጠይቃለን፡፡ የአፍሪካ ሕብረት ድርጅትም መሠረታዊ የሆኑ ሰበኣዊ መብቶችም በኢትዮጵያ ውስጥ እንዲከበሩና በሥራ ላይ እንዲውሉም ፣ጋዜጠኞችም ሥራቸውን አለ.አንዳች ቁጥጥር ተዘዋውረው እንዲሠሩ፣ ድርጅቱም ጣልቃ ገብቶ -በቻርተሩ ውል መሠረት- ተጽዕኖ እዚያ እንዲያደርግ እኛ እንጠይቃለን፡፡» ይህን ያሉት የኤሲሲኢኤሰ ናው በምጻሩ - ACCESS NOW የተባል ድርጅት ተጠሪ ወይዘሮ ፊሊሲያ አንቶኒዮ ናቸው፡፡

ምንድነው የሆነው?

ከ150 አገራት የተወጣጡ፣ወደ 300 የሚጠጉ ለሰበኣዊ መብት መከበር የሚሟገቱ የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ተሰባስበው በቅርቡ ያወጡት የጋራ መግለጫ፣ ከሓምሌ ወር ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ በኢትዮጵያ - በአማራ ክልል የኢንተርኔት መስመሮች እዚያ እንደተዘጉ ጽሑፉ መለስ ብሎ በሰነዱ ላይ ያስታውሳል፡፡ በብዙ የሚቆጠሩ ሰዎች እዚያ እንደሞቱ፣ከአንድ ሺህ በላይ ሰዎች ደግሞ በጅምላ ታፍሰው እንደ ታሰሩ - የተባበሩት መንግሥታትን ሰነድ - ማሥረጃ አድርጎ የወጣው መግለጫ የኢትዮጵያን መንግሥት ከሷል፡፡

በአማራ ክልል ጦርነቱ እንደቀጠለ ነው
በአማራ ክልል ጦርነቱ እንደቀጠለ፤ የኢንተርኔት እገዳውም ሳይነሳ ባለበት እንዳለ ነውምስል AP/picture alliance

አፍሪቃ ኢንተርኔት መዝጋት የተለመደ ነው

„በአፍሪቃ - ባለፉት ዓመታት - ግጭቶችና ጦርነቶችን በአሉበት አካባቢ - መብራት ማጥፋት እና የኢንትርኔት መስመሮችን መዝጋት እዚያ የተለመደ ነው...» ጽሑፉ ይላል፡፡ „በኢትዮጵያ ግን አሁን የሚታየው“ ወይዘሮ ፊሊሲያ አንቶኒዮ ለጣቢያችን ለዲ ደብልዩ እሳቸው እንደአሉት “ እጅግ ከሁሉም የባሰና የከፋ ነው፡፡…ለ 26 ጊዜያት በተከታታይ ፣ባለፉት ዓመታት የኢትዮጵያ መንግሥት የኢንተርኔት መስመሩን እንደአለ በአገሪቱ ውስጥ ዘግቷል…፡፡»

ለምንድነው ኢንተርኔትን የአፍሪቃ መሪዎች የሚፈሩት?

ይህን ዓይነቱን ርምጃ መንግሥት የሚወስድበት ምክንያት - መግለጫው ላይ እንደሠፈረው-  በሁለት አብይ ምክንያቶች ነው፡፡ „አንደኛው ምክንያት›- የኢንተርኔቱን መስመሩን በመዝጋት „ መግለጫው እንደሚለው. መንግሥት በገዛ ዜጎቹ ላይ የከፈተውን ጦርነት እዚያ እነሱ የሚያካሄዱትን ወንጄሎች …በፎቶና በቪዲዮ፣በድምጽ ጭምር ተቀድተው በማሥረጃ እነሱ „ -ሰነዱ እንደሚለው-  „አንድ ቀን በሕግ ፊት እንዳይከሰሱ፣ከዚያ ለማምለጥ ነው፡፡“

 የኢንተርኔት እገዳው መረጃዎችበበቂ ሁኔታ እንዳይነሸራሸሩ ገደብ ጥሏል
በአማራ ክልል ከጦርነቱ ባሻገር ከሌሎች ክልሎች በማንነታቸው የተነሳ የተፈናቀሉ በርካታ የክልሉ ነዋሪዎች ይገኛሉ ። የኢንተርኔት እገዳው መረጃዎችበበቂ ሁኔታ እንዳይነሸራሸሩ ገደብ ጥሏልምስል Alemnew Mekonnen/DW

„ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ የሰዎችን ሕይወት ለማዳን አስፈላጊና ጠቃሚ የሆኑ ዜናዎች..“ -መግለጫው እንደሚለው- „ ወደ ውጩ ዓለም እንዳይወጡ ለመቆጣጠር ነው፡፡“

ምን ይደረግ፤ ምንስ መሆን አለበት?

የወጣው የጋራ መግለጫ „በኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 29 ላይ የሠፈረው፣..የሐሳብና በነጻ አስተያየትን የማንሸራሸር መብት በአገሪቱ በኢትዮጵያ ይከበር“ ብሎ ይጠይቃል፡፡ ወረድ ብሎም ይኸው መግለጫ“ ..አንቀጽ 19 ላይ የሰፈረውን የዓለም አቀፉን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሰነድ“ ያነሳል፡፡ አንቀጽ 9 ላይ የተጻፈውን የአፍሪካ መንግሥታት የተስማሙበትን የአንድነቱን ቻርተር - ውሉን ከላይኖቹ ጋር እነዚህን ሁሉ የኢትዮጵያ መንግሥት እንዲየከብር- መግለጫው እንደገና ጠይቆ በዚህ ዓረፍተ ነገሩ ከአንባቢዎቹ እዚህ ሰሞኒን ተሰናብቷል፡፡

ይልማ ኃይለ ሚካኤል

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ነጋሽ መሐመድ