1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ፖለቲካሰሜን አሜሪካ

አሜሪካ ትግራይ የቀጠለው ጦርነት አሳስቦኛል አለች

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 6 2013

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ቃል አቀባይ ኔድ ኘራይስ ትናንት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ውጊያው ተባብሶ መቀጠሉ በትግራይ በረሃብ ለተጎዱ ነዋሪዎች የሰብዓዊ ዕርዳታ ለማድረስ የሚደረገውን ወሳኝ ጥረት የሚያደናቅፍ ነው::

https://p.dw.com/p/3wPzY
US-Außenministerium Ned Price
ምስል Nicholas Kamm/AFP/AP/dpa/picture alliance

ዩናይትድ ስቴትስ በትግራይ ክልል ተባብሶ የቀጠለው ውግያ እንዳሳሰባት አስታወቀች

ዩናይትድስቴትስ በምዕራብ ትግራይ የቀጠለው ጦርነት ከፍተኛ ስጋት እንዳሳደረባት አስታወቀች::

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ቃል አቀባይ ኔድ ኘራይስ ትናንት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ውጊያው ተባብሶ መቀጠሉ በትግራይ በረሃብ ለተጎዱ ነዋሪዎች የሰብዓዊ ዕርዳታ ለማድረስ የሚደረገውን ወሳኝ ጥረት የሚያደናቅፍ ነው:: በምዕራብ ትግራይ ቀጥሎ እየተካሄደ ባለው ውግያ ተሳታፊ ኃይሎች ለሰላማዊ ሰዎች ደህንነት ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

 ታሪኩ ኃይሉ 

ታምራት ዲንሳ

አዜብ ታደሰ