1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዲስ አበባው የተቃውሞ ሰልፍ

ሰኞ፣ ግንቦት 23 2013

በአንድ ወገን ሰልፉ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል ያሉ እንደመኖራቸው በሌላ ወገን ደግሞ ሰልፉ መካሄዱ አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የወሰደቻቸውን እርምጃዎች ቆም ብላ እንድታጤን የሚረዳ ነው በማለት የደገፉም አሉ።ሰልፉን የተቃወሙ ሁለት ፓርቲዎች ሰልፉ በኢትዮጵያ ጉዳይ የኃያላኑ ግብግብ እንዲፈጠር የሚያበረታታ ነው ሲሉ ነቅፈዋል።

https://p.dw.com/p/3uEtJ
Äthiopien Protest gegen US-Sanktionen Tigray-Krieg
ምስል Seyoum Getu/DW

አስተያየት በአዲስ አበባው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ 


ዩናይትድ ስቴትስ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ የምታደርገውን ጣልቃ ገብነት በመቃወም ትናንት በአዲስ አበባ የተደረገው ሰልፍ ላይ የተለያዩ አስተያየቶች እየተሰጡ ነው። በአንድ ወገን ሰልፉ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል ያሉ እንደመኖራቸው በሌላ ወገን ደግሞ ሰልፉ መካሄዱ አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የወሰደቻቸውን እርምጃዎች ቆም ብላ እንድታጤን የሚረዳ ነው በማለት የደገፉም አሉ።ሰልፉን የተቃወሙ ሁለት ፓርቲዎች በሰልፉ ላይ ተቃዋሚዎች ዩናይትድ ስቴትስ በውስጥ ጉዳይ እንዳትገባ ጠይቆ ሌሎች ኃያላን አገሮች ግን እንዲገቡ የመጠይቅ አዝማሚያ መታየቱ በኢትዮጵያ ጉዳይ የኃያላኑ ግብግብ እንዲፈጠር የሚያበረታታ ነው ሲሉ ነቅፈዋል።አንድ ምሁር ደግሞ  ተቃውሞን ማሰማት አሜሪካ ራሷ የምትፈቅደው መብት በመሆኑ ሰልፉ መደረጉ ተገቢ ነው ሲሉ ተናግረዋል።
ሰሎሞን ሙጬ
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ