1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አውሮጳውያን በኢራን አሜሪካ ፍጥጫ

ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 29 2012

የዩናይትድ ስቴትስ እና የኢራን ፍጥጫን ከማራገብ ይልቅ ኹኔታውን ማቀዝቀዝ እንደሚያስፈልግ አውሮጳውያን ሃገራት እያሳሰቡ ነው።  ከበርሊን ለንደን እስከ ፓሪስ ድረስ የአውሮጳ ሃገራት መሪዎች ኢራን እና ዩናይትድ ስቴትስን ወደ ውይይት ማምጣት ይገባል እያሉ ነው።

https://p.dw.com/p/3Vu6y
Iran Feier nach Raketenangriff auf US-Militärbasen im Irak
ምስል Reuters/WANA/N. Tabatabaee

ከምንም በላይ ውይይት ያስፈልጋል እየተባለ ነው

የዩናይትድ ስቴትስ እና የኢራን ፍጥጫን ከማራገብ ይልቅ ኹኔታውን ማቀዝቀዝ እንደሚያስፈልግ አውሮጳውያን ሃገራት እያሳሰቡ ነው።  ከበርሊን ለንደን እስከ ፓሪስ ድረስ የአውሮጳ ሃገራት መሪዎች ኢራን እና ዩናይትድ ስቴትስን ወደ ውይይት ማምጣት ይገባል እያሉ ነው። ሁሉም ወገን ኃላፊነቱን በአግባቡ እንዲወጣም አሳስበዋል። ሁለቱ ሃገራት ግን ከፍጥጫ ወጥተው እንዴት መወያየት ይችላሉ ለሚለው ዐቢይ ጥያቄ ግን ኹነኛ የመፍትኄ ሐሳብ እስካሁን ያቀረበ ወገን የለም። የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ኃይለሚካኤል የኢራን ዩናይትድ ስቴትስ ፍጥጫን በተመለከተ ጀርመንን ጨምሮ የአውሮጳውያኑን አቋም  በቀጣዩ ዘገባው ያስደምጠናል። 

ይልማ ኃይለሚካኤል
ማንተጋፍቶት ስለሺ
አዜብ ታደሰ