አውሮፓ በ2024 እንዴትና ወዴት
ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 15 2017አውሮፓ በ2024 እንዴትና ወዴት
ጎርጎሮሳዊው 2024 ዓመት ምኅረት በአውሮፓ በርካታ የኢኮኖሚ ፖለቲካዊና ወታደራዊ ክስተቶች የታዩበት ነው። የየተፈጥሮ አደጋዎችም የተከሰቱበት፤ ከሁለተኛው አለም ጦርነት ወዲህ ከፍተኛ የደህንነት ስጋት የተጋረጠበት፤ የጦርነት ዳመናም ያንዣበበት ዓመት ነው። በርካታ የህብረቱ አገሮች ምርጫ ያካሄዱበትና መንግስቶቻቸውን የለወጡበትም ነበር። የኑሮ ውድነቱና የዋጋ ግሽበቱም ከመቼውም ግዜ ይበልጥ ያሻቀበበት፤ ስደተኞች ወደ ህብረቱ እንዳይገቡ ለመክላከልና የገቡትንም መልሶ ለመላክ የሚያስችሉ ህጎችና ደንቦች የወጡበትና የደንበር ቁጥጥሩ ያየለበት ዓመትም ነበር 2024 ዓም።
የአውሮፓ 2024 ምርጫዎች ውጤት
2024 በአውሮፕ የምርጫ አመት ነበር ማለት ይችላል። ጥቂት የማይባሉ የህብረቱ አባል ገሮች ብሄራዊና አካባቢያዊ ምርጫዎች አካሂደው መንግስቶቻቸውን ለውጠው ባብዛኛው ጥምር መንግስቶችን መስርተዋል። አመቱ በየአምስት አመቱ የሚካሄደው የአውሮፓ ፓርላማ ምርጫ የተከሄደበትና ውጤቱም በአይነቱ ከቀድሞዎቹ የተለየ የሆነበት ነበር። እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከስኔ 6-9 በ27ቱ አገሮች በተካሄደው ምርጫ ባልተለመደ ሁኔታ ብሔረተኛና ስደተኛ ጠል የሆኑ ፓርቲዎች አሸናፊዎች ሆነው ወጥተዋል። ይህም በተለይ በጀርመንና ፈርንሳይ ጎልቶ የታየ ሲሆን በንዘርላንድስ፣ ኦስትሪያ ክሮሺያ ሀንጋሪ ጣሊያን፣ በመሳሰሉ አገሮች ቀኝ አክራሪ ኃይሎች በጥምር አገሮቻቸውን እየመሩ ነው ። በአጠቃላይ በአመቱ በተለያዩ አባል አገሮችም ሆነ በአውሮጳ ድረጃና በተለይም በአውሮጳ ፓርላማ በተካሄደው ምርጫ የመሀል ቀኙ ፓርቲ ትልቁ ፓርቲ ይሁን እንጂ፤ የአክራሪ ቀኝና ብሄረተኛ ፓርቲዎቹ ነባሮቹን የሶሊስቶች ሊበራሎችና አርነጓዴዎቹን ፓቲዎች በልጠው ተጽኖ ፈጣሪ ብቻ ሳይሆኑ ገዥ ፓርቲዎችም ለመሆን በቅተዋል።ብዙዎቹ እነዚህ ፓርቲዎች ቀደም ሲል የነበራቸውን የፀረ አውሮፓ ህብረት አቋሞች በማለዘብ፤ህብረቱ እንዲቀጥል፤ ግን መርሆቹና አሰራሮቹ እንዲየየሩ ወይም እንዲሻሻሉ እንደሚፈልጉና እንደሚታገሉ ነው በአሁኑ ወቅት የሚሰማው። በመሆኑም በዚህ አመት በየአገሩቹና በአውሮፓ ፓርላማ በርካታ መቀመጫዎችን ያገኙት የቀኝ አክራር ፓርቲዎች ከእንግዲህ ተቃዋሚዎች ብቻ ሳይሆኑ ተጽኖ ፈጣሪዎችና አቅጣጫ ለዋጮች ሊሆኑ እንደሚችሉ ነው ብዙዎች የሚያምኑት። በብራስልስ የዲደብሊው ዘጋቢዋ ክርስቲን ምሁንድዋ እንደምትለው “አክራሪዎቹ ፓርቲዎች አውሮፓ ህብረት ጉዳይ የተለየ አመላከክት ነው ያላቸው። በስደተኖች ጉዳይ ይሁን ወይም በዩክሬን ጦርነት ወይም በአየር ንበረት ለውጥ ላይ፤ የተለየ አረዳድ ነው ያላቸው”። በመሆኑንም የእነዚህ ፓርቲዎች በየደረጃው እየጎልበቱ መምጣት ወደ ፊት ህብረቱ በስደተኖችም ይሁን በዩክሬን ጦርነት ወይንም በአየር ንብረት ላይ ጠንካራ አቋም የሚያራምዱ ተጽኖ ፈጣሪ ኃይሎች መሆናቸው የማይቀር ነው።»ከሀማስ ጥቃት በኋላ የአውሮጳ ኅብረትና የእሥራኤል ግንኙነት ይዞታ
የቀኝና ብሄረተኛ ሀይሎች አሸናፊ የሆኑባቸው ምክኒያቶች
በአጠቃላይ የዘንድንሮው ምርጫ አውሮጳን ከመቺውም ግዜ ይበልጥ ወደቀኝ እንዲያጋድል አድርጎታል። ይህ እንዴት ሊሆን እንደቻለ የ ሚገልጹ የተለያዩ ትንታኔዎችና አስተያየቶች ቢሰጡም፤ ህዝቡ በነባሮቹ ፓርቲዎች በመሰላቸቱና ኑሮም እየከበደው በመምጣቱ አማራጭ በመሻት እንደሆነ ግን ብዙዎች ያምናሉ። ከሁሉም በላይ ግን ለወትሮው ድምጹን ለአረንጓዴዎቹና የግራ ፓርቲዎች ይሰጥ የነበረው ወጣት በአሁኑ ወቅት ላአክራርዊቹና ብሄረተኞቹ ድጋፉን በማሳየቱ ምክኒያት እንደሆነ ነው የህዝብ አስተያየትን የሚከታተሉ ባለሙያዎች በጥናቶቻቸው ያመላከቱት።
በ2024 የተሾሙ የአውሮፓ ህብረት ተቋማት መሪዎች
በዚህ የምርጫ ውጤት መሰረትም የአውሮፓ ፓርላማ የህብረቱን ዋና ዋናና ተቋሞች መሪዎች ሹሟል። የፓርላማውንና የኮሚሽኑን ፕሬዝደትነት ወይዘሮ ሮበርታ ሜትሶላ እና ወይዘሮ ኡርሱላ ቮንዴር ለየን ሁለቱም ክመሀል ቀኙ ያውሮፓ ህዝብ ፓርቲ በድጋሚ ይዘዋል። ቀድሞ የኢስቶኒያ ጠቅላይ ሚኒስተር የነበሩት ወይዘሮ ካያ ክላስ ከሊበራሎቹ ፓርቲ የውጭ ግንኑነት ሀላፊነቱን እንዲይዙ የተደረገ ሲሆን፤ ካውንስሉን ላለፉት አራት አመታት በፒረዝዳንትነት የመሩትን ቻርለስ ሚሸልን ደግሞ ቀድሞ የፖርቱጋል ጠቅላይ ሚኒስተር የነበሩትን ሚስተር አንቶኒዮ ኮስታን ካውንስሉ ሊራዘም ለሚችል የሁለት አመት ግዜ ሹሟቸዋል።፡እናም 2024 ለአውሮፓ ህብረት አዲስ ፓርላማ ብቻ ሳሆን አዳዲስ ሹሞችንም አምጥቷል።፡
የህብረቱ እጩ አባሎችና ብሪታኒያ
ህብረቱ በዚህ አመት ወደ ህብረቱ ለመግባት የፈለጉ ተጨማሪ አገሮችንም በተለያየ ደርጃ በእጩነት ተቀብሏል። ቱርክን ጭምሮ ሰባት አገሮች በእጩ አባል አገሮች ዝርዝር ውስጥ የሚገኙ ሲሆን ዩክሬንና ሞልዶቫም እጩ አባሎች እንዲሆኑንና በተለየ ሁኔታ ዩክሬን የመግቢያ ድርድሩን እንድትጀምር የተፈቀደ መሆኑ ታውቋል። የህበረቱ አባል ለመሆን መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች ያሉ ሲሆን፤ መስፈርቶቹ መሟላታቸውን ለማረጋገጥም በህብረቱና በእጩዎቹ አገሮች መካከል የሚደረጉ ድርድሮች በርካታ እርከን ያላቸውና ብዙ ግዜም የሚፈጁ እንደሆነ ነው የሚታወቀው።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ በብርታኒያ የመንግስት ለውጥ መደረጉን ተከትሎ የነበረውን ግንኑነት ለማሻሻል ንግግሮች መጀምራቸውም ተገልጿል። አሁን በስልጣን ላይ ያለው የሌበር መንግስት ምንም እንኳ ቀደም ብሎ ብርታኒያ ከህብረቱ እንድትወጣ የማይፈልግ እንድነበር ቢታወቅም፤ የአሁኑ እንቅስቃሴ ግን ከህብረቱ ጋር ያለውን ድህረ ብሬክዚት ግንኙነትን የበለጠ ለማሳለጥ እንጂ ብርታኒያን ቢያንስ አሁን እንደገና ወደ ህብረቱ ለመመለስ እንዳልሆነ ነው የሚታመነው። ሆኖም ግን ባሁኑ ወቅት ሁለቱ ወገኖች ግንኑነታቸውን ለማሻሻል በከፍተኛ ፍላጎትና ስሜት እየሰሩ መሆንቻቸውን አዲሱ የካውንስሉ ፕሬዝዳንት ሚስተር አንቶኒዮ አስታውቀዋል።
የኢኮኖሚው ሁኔታ
2024 ለአውሮፓ ህብረት አዳዲስ የፖለቲካ ሀይሎች ወደ ስልጣን የመጡበት ብቻ ሳይሆን ጀርመንን ጨምሮ በበርካታ የህብረቱ ደባባዊና ምስራቃዊ አገሮች የተፍጥሮ አደጋ የደረሰበትና በተለይም የጎርፍ መጥልቅለቅ ያጋጠመበትም አመት ነበር።፡።፡
በኢኮኖሚው ዘርፍ 2024 በአውሮፓ ብዙም እድገት ያልታየበትና ይልቁንም የዋጋ ንረትና የኑሮ ውድነት ያሻቀበበት አመት መሆኑ ግልጽነው። የዩኪረን ጦርነት የፈጠረው የኢኮኖሚ ቀውስ፤ የጂፖለቲካ ውጥረቶች እንዲሁም የህብረቱ ተወዳደሪነት እየቀነሰ መሄድን ባለሟይዎች ለኢኮኖሚው ማዝገምና ማዝቆልቆል፤ ብሎም ለኑሮ ውድነት እንደ ምክኒያት ከሚጠቅሷቸው ውስጥ ናቸው ። የሰደተኖችና ፈላስያን በብዛት ወደህብረቱ መግባትም ሊከኦኖሚና ማህበራዊ ችግሮች እንደምክኒያት የሚነሱ ሲሆን ከበርካታ አመታት ድርድር በኋላም በዚህ አመት የህብረቱ የጋራ የስደተኖች ያቀባበልና አይያዝ መመሪያ ጸድቋል።፡
የስደተኖች የጋራ መመሪያ መጽደቅና ተቃውሞው
ባለፈው ሰኔ የጸደቀው የየህብረቱ የስደተኖች የጋራ መመሪያ አውሮፓ ያለማቀፍ የስደተኖችና ሰባዊ መብት ድንጋጌዎችን በመጣስ ለተገን ጠያቂዎችና ድጋፍ የሚፈልጉ ጉዳተኖች በሩን እንዲዘጋ የሚፈቅድ ነው በማለት የሰባዊ መብት ድርጅቶች ተቃውመውታል።ሆኖም ግን ብዙዎቹ አባል መንግስታት ወደ ስልጣን የመጡት በዋናነት በስደተኖች አጀንዳ በመሆኑ መመሪያው ተግባራዊ እንደሚሆንና መጭው ግዜም ወደአውሮፓ ለመግባት ለሚፈልጉም ሆነ ለገቡ ስደተኖች ጥሩ እንደማይሆን ነው ነው በብዙዎች የሚታመነው።፡
የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት የፈጠረው ስጋት
በሌላ በኩል ሩሲያ በዩክሬን የከፍተችው ጦርነት አውሮፓን ከሁለተኛው አለም ጦርነት ወዲህ የስጋት ምድር እንድትሆን እድርጉታል እየተባለም ነው።፡ጦርነቱ በዚህ አመት በህብረቱ ላይ በኢኮኖሚ ካስክተለው ችግር ባለፈ በአህጉሩ የደህንነት ስጋት ፈጥሯል፤የጦርነት ዳመናም እንዲያንዣብብ አድርጓል። የህብረቱ አባል ገሮችና አብዛኞቹ የህብረቱ አገሮች አባል የሆኑበት የስሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) በጦርነቱ በቀጥታ ከመሳተፍ በመለስ የወታደራውና ፋይናንስ ወጭዎች ዋናዎቹ ባለቤቶች ናቸው። ይህ አውዳሚ ጦርነት ከዚህን ያህል ግዜም በሁዋላ ሊያበቃ የሚችልበት ሁኒታ እየታየ እለመሆኑ፤ አውሮፓን ከከፋ የኢኮኖሚ ቀውስ በላይ የጦርነት ስጋትም እንዲጋረጥበት አድርጓል። ያም ሆኖ ግን ህብረቱ ዩኪረንን በአሸናፊነት እንድትወጣ ከማድረግ ውጭ አማራጭ እንሌለው በማመን እርዳታ ድጋፉን አጠናክሮ ለመቀጠል የወሰነ መሆኑን ነው የህብረቱ ፕሬዝዳንት ሚስተር አንቶኒዮ ባለፈው ሀሙስ ከመሪዎቹ ጉባኤ በኋላ ያስታወቁት፤ “ ያውሮፓ ህብረት ዩክሪን አጠቃላይና ዘላቂ ሰላሟ እስከሚረጋገጥ ድረስ ድጋፉን ይቀጥላል” በማለት አሁን ግዜው የሰላም አማራጭ ሀሳቦች የሚውጠነጠኑበት ሳይሆን ዩክሬንን ማጠናከር የሚያስፈልገበት ወቅት መሆኑን አስገንዝበዋል ።ዩክሬንና መካከለኛው ምሥራቅ ላይ ያተኮረው የአውሮጳ ኅብረት ሚኒስትሮች ስብሰባ
ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለአውሮፓ ስጋት ወይንስ ተስፋ
ሆኖም ግን ከሁለት ሳምንት ባሁላ ኋይት ሀውስን የሚረክቡት ተመራቹ ፕሬዝዳንት ሚስተር ትራምፕ ጦርነቱ መቆም እንዳላለበት በመጠየቅ ለዩክሬን የሚሰጡት እርዳታ ቢያንስ በነበረው ሁኒታ ማስቀጠል እንደማይፈልጉ አስታውቀዋል። የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ዚለንስኪ ባለፈው ሀሙስ ብራስልስ እንደገለጹት ደግሞ የአሜሪካ ድጋፍ አስፈላጊና ወሳኝም ነው፤ “ ለዩክሬን ደህንነት የአውሮፓውያን ድጋፍና ዋስትና ብቻውን በቂ አይደለም፤ ምክኒያቱም ዛሬም ሆነ ወደፊት ዋና አጋርና ዋስትና ሊሆን የሚችለው የስሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ነቶ) ነው” በማለት ያሜሪንን ድጋፍ ወሳኘት አጽናኦት ስተው ተናግረዋል ተማጽነዋልም።፡
የዩኤስ ምርጫ ለአውሮጳውያን አንደምታው፦ ቃለ መጠይቅ
ኔቶ በዚህ አመት ስዊድንና ፊንላንድ በመጨመር በእለማችን ትልልቁ ወታደራዊ ኃይል ቢሆንም ዋናዋ ኃይል ግን አሜሪካ ናት፡፤ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ግን ቀደም ሲልም በኔቶ አባል አገሮች ተዋጾ ቅሬታ የነበራቸው ሲሆን፤ የአሚሪካንን ተሳትፎ ለማስቀጠልና ለማሳደግ የዩክሬንን ጦርነት ማስቆምን ጨምሮ ሌሎች ቅድመሁኒታዎችን ሳይስቀምጡ እንደምይቀሩ ነው ብዙዎች በስጋት የሚናገሩት፡፤ ከበርኒንግ ሃም ዩንቨርስቲ ፕሮፊሰር ዳቪድ ዱን እንደሚሉት ለውሮፓ ደህንነት ትልቁ አሳስቢ ጉዳይ ፕሬዳንት ትራምፕ በዩክሬን ጉዳይ የሚወስኑት ውሳኔ ነው እሳቸው “ የትርማፕ ወደ ስልጣን መምጣት ነባሩን የአትላንቲክ ማዶና ማዶ ግንንኙነት ሊያቀዘቅዘውና ሊቀይረውም ይችላል”; ይህ ክሆነ ደግሞ አውሮፓ ለዩክሬን ደህንነት ዋስትና የሚሰጥ ሳይሆን ለራሱም የደህንነት ስጋት ያለበት ሊሆን እንደሚችመል ነው በብዝዎች የሚነገረው።
ከዚህ በተጨማምሪም የፕሬዝዳንት ትራምፕ መመረጥ ለአውሮጳ በርክታ ተግዳሮችቶችንና ፈተናዎችን ይዞ ሊመጣ ኧንደሚችል ነው እየተገጸለ ያለው። በምርጫ ዘመቻቸው ወቅትም ይሁን አሁን ሲናገሩ እንደሚሰሙት ከአውሮፓ ወደ አሜርሪካ በሚገቡ ሽቀጦች ላይ እስከ 20 ከመቶ ሊደርስ የሚቺል ቀረጥ ሊጥሉ ይችላሉ፤ ከፓሪሱ የአየር ንብረት ስምምነትም ሊወጡ ይቻላሉ። ይህ ሁሉ እየሆነ ያለውና የሚሆነው ደግሞ የህብረቱ ዋና ሞተሮች የሆኑት ጀርመንና ፈርንሳይ የፖለቲካ ቀውስ ውስጥ በገቡበት ወቅትና ለጊዜውም ቢሆን በሁለትም አገሮች ጠንካራ ውሳኔ ሰጭ መንግስታት በሌሉበት መሆኑ የአውሮጳን መጻኢ ግዜ አሳስቢ አድርጎታል። ይህ ሁሉ ተዳምሮም ለአውሮጳ መጭው 2025 አመትም የፈተናና ተግዳሮት ግዜ እንዳይሆን ያሰጋል ነው የሚባለው።
ገበያው ንጉሴ
ኂሩት መለሰ